አጣሪ ጉባዔው በ67 ጉዳዮች ላይ ውሳኔ አሳለፈ
March 7, 2023
Show all

ጉባዔው በ37 ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ

????????????????????????????????????

የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ ባካሄደው ጉባዔ ቀደም ሲል በተለያዩ ጊዜያት በጉባዔና በንዑስ ጉባዔ ደረጃ ሲመረምራቸው ከቆያቸው አቤቱታዎች መካከል በ37 ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ።

አጣሪ ጉባዔው ሐሙስ መጋቢት 7 ቀን 2015 ዓ.ም ባደረገው መደበኛ ጉባዔ 37 የባለጉዳይ አቤቱታዎችን መርምሮ አንድ ጉዳይ የሕገ መንግሥት ትርጉምያስፈልገዋል በማለት ወደ ፌዴሬሽን ምክር ቤት እንዲላክ ሲወስን ሁለት ጉዳዮች ደግሞ የመጨረሻ ውሳኔ ከመተላለፉ በፊት ተጨማሪ መረጃ ለማጣራት እንዲቻል ተጠሪዎች መልስ እንዲሰጡበት ትእዛዝ ተላልፏል፡፡  ቀሪዎቹ 34  መዝገቦችን ግን የሕገ መንግሥት ጥሰት የሌለባቸው እንደሆኑ ጉባዔው በማጣራት ሂደቱ ስላረጋገጠ የሕገ መንግሥት ትርጉም አያስፈልጋቸውም የሚል ውሳኔ በመስጠት ዘግቷቸዋል።

ጉባዔው ሰፊ ውይይት ካካሄደ በኋላ ትርጉም ያስፈልገዋል ብሎ ለመጨረሻ ትርጉም ወደ ፌዴሬሽን ም/ቤት እንዲላክ የወሰነው ጉዳይ በመዝገብ ቁጥር 2548/10 የቀረበ የንብረት መብት ሕገ መንግሥታዊ ጉዳይን የሚመለከት ሲሆን አመልካች የተከራከሩበትን የመኖርያ ቤት በተመለከተ በጠቅላይ ፍርድ ቤት በእርቅ ስምምነት የዘጋውን ጉዳይ የእርቅ ውሉ ያልተመዘገበ ነው በማለት ፍርድ ባለመፈፀሙ በሕገ መንግስቱ የተረጋገጠልኝ የንብረት መብቴ ተጥሷል በሚል ያቀረቡት አቤቱታ ነው፡፡ ጉባዔውም በጉዳዩ ላይ በስፋት ከተወያየ በኋላ የፌደራል ጠ/ፍ/ቤት በእርቅ ስምምነት የሰጠውን ፍርድ የፌደራል የመ/ደ/ፍ/ቤት  ማስፈጸም ሲገባው ያንን በመተው ቀደም ሲል የፌ/ከ/ፍ/ቤት የሰጠውን ፍርድ ማስፈጸሙ የአመልካችን የንብረት መብት የሚጥስ በመሆኑ የሕገ መንግሥት ትርጉም ያስፈልገዋል በማለት ለመጨረሻ ውሳኔ ወደ ፌዴሽን ም/ቤት እንዲላክ ወስኗል፡፡

በተጨማሪ ሰፊ ውይይት ከተደረገባቸው ሁለት ጉዳዮች አንዱ በመዝገብ ቁጥር 5234/12 የንብረት መብት ሕገ መንግሥታዊ ክርክር ሲሆን አመልካቾች አከራካሪውን ቤት በውክልና ሰጥተው ከሄዱ በኋላ በተወካዩ አማካኝነት ያለአግባብ ለሶስተኛ ወገን የተሸጠብኝ ቤት ተመልሶ ይሰጠኝ የሚል ነው፡፡  ጉባዔውም የንብረት መብት ጥበቃ መደረግ ያለበት የሚጠበቅባቸውን አሟልተው ለገዙ የ3ኛ ወገን  ነው ወይስ  ቀደም ሲል ንብረታቸው ያለአግባብ የተሸጠባቸው ባለንበረት በሚለው ላይ  በስፋት በመወያየት ለተጨማሪ መረጃ ተጠሪዎች መልስ እንዲሰጡበት ትእዛዝ አስተላልፏል፡፡ ሁለተኛውና በመዝገብ ቁጥር  5542/13 የተመረመረተው ጉዳይ ከፌደራልና ከክልል ፍ/ቤቶች የስልጣን ወሰን ጋር በተያያዘ የግንባታ ውል ክርክርን በሚመለከት የቀረበ ሲሆን በዚህም ጉዳይ ተጨማሪ ማጣራት ተደርጎ ተጠሪዎች መልስ እንዲሰጡበት ታዟል፡፡