አጣሪ ጉባዔው በ67 ጉዳዮች ላይ ውሳኔ አሳለፈ
March 3, 2023
ጉባዔው በ37 ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ
March 17, 2023
Show all

አጣሪ ጉባዔው በ67 ጉዳዮች ላይ ውሳኔ አሳለፈ

የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ የካቲት 23/2015 ባካሄደው መደበኛ ጉባዔው ቀደም ሲል በዋናና ንዑስ ጉባዔ ደረጃ ሲወያይባቸው የነበረውን 67 የባለጉዳይ አቤቱታዎችን መርምሮ 65ቱ ጉዳዮች የሕገ መንግሥት ጥሰት የሌለባቸው ሆኖ ስላገኛቸው ውሳኔ በመስጠት ዘግቷቸዋል። ቀሪ ሁለት መዝገቦች ላይ ከመጨረሻ ውሳኔው በፊት ተጨማሪ መረጃዎችን ለማጣራት እንዲቻል በተጠሪዎች ምላሽ እንዲሰጥባቸው ትዕዛዝ አስተላፏል።ጉባዔው የሕገ መንግሥት ትርጉም አያስፈልጋቸውም በማለት ውሳኔ ካሳለፈባቸው ጉዳዮች መካከል በሦስቱ ላይ ከፍተኛ ክርክር ካካሄደ በኋላ በመጨረሻም የሕገ መንግሥት ጥሰት የለባቸውም የሚል ውሳኔ ላይ ሊደርስ ችሏል።የተጠሪ ምላሽ እንዲሰጥባቸው ትዕዛዝ ከተላለፈባቸው ሁለት ጉዳዮች አንዱ፣ በአንድ የኅብረት ሥራ ሽርክና ማኅበር አመልካችነት በሕገ መንግሥቱ ከተደነገጉ መብቶች መካከል 3 የሚሆኑ መብቶቼን ማለትም፡- የመደራጀት መብት (አ.31)፣ ፍትህ የማግኘት መብት (አ.37) እና በአንቀፅ 78 ስለ ነፃ የዳኝነት አካል በሚል ከተዘረዘሩ ድንጌዎች መካከል ያሉት ተጥሰውብኛልና ትርጉም ይሰጥልኝ በሚል ለጉባዔው የቀረበ አቤቱታ ነው።ሁለተኛው ጉዳይ የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ከተጠሪዎች ጋር ባደረኩት የፍርድ ቤት ክርክር በፍርድ ቤቶች የተሰጠብኝ ውሳኔ በሕገ መንግሥቱ አንቀፅ 37 የተደነገገውን ፍትህ የማግኘት መብቴን የጣሰ ስለሆነ ጉባዔው ትርጉም ይስጥልኝ ሲል ለጉባዔው የቀረበ አቤቱታ ነው።በእነዚህ አቤቱታዎች ላይ ጉባዔው ሰፊ ውይይት በማድረግ አመልካቾች ተጥሰውብኛል ያሏቸውን መብቶች ከሕገ መንግሥቱ ድንጋጌዎች አንፃር ከመረመረ በኋላ የሕገ መንግሥት ጉዳይ ሊኖርባቸው ይችላል የሚል ዕምነት በማሳደሩ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማጣራት በአዋጅ ቁጥር “798/2005” እና በጉባዔው “የጉዳዮች አቀራረብና አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 1/2012” መሰረት ተጠሪዎች ምላሽ እንዲሰጡ ትዕዛዝ በመስጠት የዕለቱን መደበኛ ጉባዔ አጠናቋል።