የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ አዲስ ሶፍት ዌር ከቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ተረከበ
December 2, 2019
የሃዘን መግለጫ:-የቀድሞው የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዚዳንትና የሕገ መንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ ሰብሳቢ የነበሩት ክቡር አቶ ተገኔ ጌታነህ ህዳር 22 ቀን 2012 ዓ.ም ከዚህ አለም በሞት በመለየታቸው የሕገ መንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ ፅ/ቤት ሀላፊዎችና ሰራተኞች የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን እየገለፁ ለቤተሰቦቻቸውና ለስራ ባልደረቦቻቸው መፅናናትን ይመኛሉ፡፡
December 2, 2019

ጉባዔው ከሕገ መንግሥት አተረጓጎም ጋር ተያይዞ በተሰጡ ጉዳዮች ላይ ከኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ዳኞች ጋር ተወያየ

????????????????????????????????????

ጉባዔው ከሕገ መንግሥት አተረጓጎም ጋር ተያይዞ በተሰጡ ጉዳዮች ላይ ከኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ዳኞች ጋር ተወያየ

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ ከኦሮሚያ ብ/ክ/መ ጠቅላይ ፍ/ቤቶች ዳኞች ጋር ከሕገ መንግሥት አተረጓጎም ጋር ተያይዞ በተሰጡ ጉዳዮች ላይ ህዳር 19 እና 20 ቀን 2012 ዓ.ም በቢሾፍቱ ከተማ ውይይት አካሄደ።

በውይይት መድረኩ መክፈቻ ላይ የኦሮሚያ ብ/ክ/መ ጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዚዳንት ክቡር አቶ ደሳ ቡልቻ በሕገ መንግሥት መሰረታዊ መርሆችና ከሕገ መንግሥት አተረጓጎም ጋር ለተያያዙ ጉዳዮች በምን መልኩ ትርጉም ይሰጣል በሚለው ላይ ከመድረኩ የተሻለ ግንዛቤ ለመያዝ ያስችላል ብለዋል።

የሕገ መንግሥት ጉዳይ ለዳኞች በዕለት ተዕለት ስራቸው ውስጥ ያለ መሆኑን ጠቁመው ዳኞች ሕግ በሚተረጉሙበት ወቅት የሚያጋጥሙ ችግሮችንና መፍትሄዎቻቸውን በምን መልኩ ማስኬድ እንዳለባቸው የሚረዳ መድረክ በመሆኑ በትኩረት ተሳትፎ ማድረግ እንደሚጠበቅ ተናግረዋል።

በተለይ በሕገ መንግሥት ዙሪያና ውሳኔ በተሰጠባቸው ጉዳዮች ላይ በመድረኩ ላይ የነቃ ተሳትፎ በማድረግ በሕገ መንግሥት አተረጓጎም ላይ የተሻለ ግንዛቤ መጨበጥ እንደሚቻል፣ እንዲሁም የዳኞች ሚና እና የሕገ መንግሥት ተርጓሚው አካል ሚና ምን እንደሆነ ለመረዳት እንደሚጠቅም አመልክተው የውይይት መድረኩ የተሳካ እንዲሆንና ሁሉም በትኩረት እንዲሳተፍ አሳስበዋል።

በዕለቱም በሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ ጽ/ቤት ኃላፊ በአቶ ደሳለኝ ወዬሳ የሕገ መንግሥት አተረጓጎም መሰረታዊ መርሆች፣ በአጣሪ ጉባዔው ጽ/ቤት የሕገ መንግሥት አስተምህሮ ቡድን መሪ በአቶ ያደታ ግዛው የገጠር መሬት ስለሚተላለፍበት አግባብ ከኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሕገ መንግሥት አንጻር፣ እንዲሁም በኦሮሚያ ብ/ክ/መ ጠቅላይ ፍ/ቤት ዳኛ በአቶ ዶቤ ዳባ ከገጠር መሬት ጋር ተያይዞ የሚነሱ ክርክሮችና የተሰጡ የፍ/ቤት ውሳኔዎች በሚል ጽሁፎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል።

በሁለተኛው ቀንም በኦሮሚያ ብ/ክ/መ ሕገ መንግሥት አጣሪ ኮሚሽን ጽ/ቤት ኃላፊ በአቶ ደሞዜ ማሜ የሕገ መንግሥት ጉዳዮችን ከመደበኛ ፍ/ቤት የመለየት ሥራ በኦሮሚያ ሕገ መንግሥት አጣሪ ኮሚሽን ተሞክሮ፣ እና በሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ ጽ/ቤት የጥናትና ምርምር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በአቶ ጌታቸው ጉዲና ሳይፋቱ ፍቺ ወይም በሁኔታ ስለመለያየት እንዲሁም ከአንድ በላይ ጋብቻ በሚኖርበት ጊዜ የንብረት ክፍፍልን የሚመለከት ጥናታዊ ጽሁፎች ቀርበው ውይይት ከተደረገባቸው በኋላ የዕለቱ የውይይት መድረክ ተጠናቋል።