ማርች 8
March 6, 2020
   ማስታወቂያ
March 25, 2020

ጉባዔው ከሕገ መንግሥት አተረጓጎም ጋር በተያያዘ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ጠቅላይ ፍ/ቤት ዳኞች ጋር የግንዛቤ ማስጨበጫ ውይይት አካሄደ

????????????????????????????????????

ጉባዔው ከሕገ መንግሥት አተረጓጎም ጋር በተያያዘ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ጠቅላይ ፍ/ቤት ዳኞች ጋር የግንዛቤ ማስጨበጫ ውይይት አካሄደ

=============================================

የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ ከሕገ መንግሥት አተረጓጎም ጋር በተያያዘ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ጠቅላይ ፍ/ቤት ዳኞች ጋር መጋቢት 05 እና 06/ 2012 በክልሉ ርዕሰ ከተማ አሶሳ በመገኘት የሁለት ቀናት የግንዛቤ ማስጨበጫ ውይይት አካሄደ።
በጉባዔ አባላትና በጉባዔው ጽ/ቤት የሕገ መንግሥት ከፍተኛ ተመራማሪ ባለሙያዎች አማካይነት የመወያያ ፅሑፎች ቀርበው ውይይት ተካሂዶባቸዋል። “የሕገ መንግሥት አተረጓጎም መሰረታዊ መርሆዎች”፣ “ፍትህ የማግኘት መብት ከኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት አንፃር”፣ “ከፍርድ ቤት የሚላኩ የሕገ መንግሥት ትርጉም ጥያቄዎች ምንነትና አተገባበር” እና “የፍርድ ቤት ነፃነት ከኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት አንፃር” የሚሉ አራት ፅሑፎች ቀርበው ከታሳታፊዎች ጋር ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡
በተጨማሪም ጉባዔው ለፌዴሬሽን ምክር ቤት የውሳኔ ሀሳብ ያቀረበባቸው የተመረጡ ጉዳዮች ቀርበው ሰፋ ያለ ውይይት የተካሄደባቸው ሲሆን፣ ጥያቄና አስተያየትም ቀርቦባቸው በአቅራቢዎቹ ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል።
በግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኩ ላይ የክልሉን ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚደንት ክቡር አቶ አብዲሳ ዋሴ እና አፈ ጉባዔውን ጨምሮ የጠቅላይ ፍርድ ቤቶች ዳኞችና የተለያዩ የሥራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ተገኝተው ተሳትፈውበታል፡፡

????????????????????????????????????

????????????????????????????????????

????????????????????????????????????