በሩስያ አስተናጋጅነት እየተካሄደ በሚገኘው የብሪክስ አባል ሀገራት የጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዝዳንቶች ጉባዔ ኢትዮጵያ በክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት በመወከል እየተሳተፈች ትገኛለች።
June 18, 2024
ጉባዔው በ43 የሕገ መንግሥት አቤቱታዎች ላይ ብይን ሰጠ።
June 21, 2024
Show all

ጉባዔው በ80 የአቤቱታ መዛግብት ላይ ተወያይቶ ውሳኔ እና አቅጣጫ አስቀመጠ።

????????????????????????????????????

የኢፌዴሪ የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ ሐሙስ ሰኔ 6 ቀን 2016 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ በንዑስ አጣሪ ጉባዔ እና በአጣሪ ጉባዔ ጽ/ቤቱ የሕግ ተመራማሪዎች ሰፊ ማጣራት ተደርጎባቸው ለውሳኔ ከቀረቡለት የሕገ መንግሥት የትርጉም አቤቱታዎች መካከል 80 በሚሆኑት ላይ ተወያይቶ ውሳኔ እና አቅጣጫ አስቀምጧል።

 በዚህ 77 በሚሆኑ የሕገ መንግሥት ትርጉም አቤቱታዎች ላይ በስፋት ተወያይቶ የሕገ መንግሥት ጥሰት አልተፈፀመባቸውም በማለት የሕገ መንግሥት ትርጉም አያስፈልጋቸውም የሚል ውሳኔ ሲያሳልፍ ሌላ አንድ መዝገብ ላይ ተጨማሪ ማጣራት ተደርጎበት በቀጣይ ለውሳኔ እንዲቀርብ አቅጣጫ ተሰጥቶበታል፡፡

በሌላ በኩል ከጋብቻ ፍቺ ጋር በተያያዘ ፍትህ የማግኘት ሕገ መንግሥታዊ መብትን የሚመለከት ሌላ አንድ መዝገብ ላይ ከተወያየ በኋላ በተጠሪ መልስ እንዲሰጥበት ትእዛዝ ሰጥቷል ።