የመደራጀት መብት በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሕገ መንግሥት
January 5, 2023

ጉባዔው በ70 ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ

የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ ረቡዕ ታህሳስ 26 ቀን 2015 ዓ.ም ባካሄደው ጉባዔ ቀደም ሲል በተለያዩ ጊዜያት በጉባዔና በንዑስ ጉባዔ ደረጃ ሲመረምራቸው ከቆያቸው አቤቱታዎች መካከል በ70 ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ።

አጣሪ ጉባዔው በታህሣስ 26/2015 መደበኛ ጉባዔው 70 የባለጉዳይ አቤቱታዎችን መርምሮ 70ዎቹም መዝገቦች የሕገ መንግሥት ጥሰት የሌለባቸው ሆኖ ስላገኛቸው የሕገ መንግሥት ትርጉም አያስፈልጋቸውም የሚል ውሳኔ በመስጠት ዘግቷቸዋል።

ከ70ዎቹ ጉዳዮች 68ቱ ምንም ዓይነት የሕገ መንግሥት ጥሰት የሌለባቸው እንደሆኑ ጉባዔው በማጣራት ሂደቱ ስላረጋገጠ ያለምንም ልዩነት በቀጥታ እንዲዘጉ ሲወስን፣ ቀሪ ሁለት መዝገቦች ግን ሰፋ ያለ ክርክር አድርጎባቸዋል።

እነዚህም ሁለት ጉዳዮች እንደባልና ሚስት አብሮ የመኖር ግንኙነት ጋር በተያያዘ  የንብረት ድርሻ ክፍፍል ጥያቄን የተመለከተው ጉዳይ አንዱ ነው፡፡ በዚህም ጉዳይ ጉባዔው በስፋት ከተወያየ በኋላ እንደባልና ሚስት የመኖር መሰረቱ አብሮ መኖር እንደሆነና ግንኙነቱም በንብረት ረገድ ውጤት ሊያስከትል የሚችለው ግንኙነቱ ያልተቋረጠ ከሆነ ነው፡፡ በተያዘው ጉዳይ ደግሞ አመልካችና ተጠሪ እንደባልና ሚስት በነበራቸው ግንኙነት ወቅት የተፈራ ንብረት ያለመኖሩ በግራቀኙ የታመነ ነው፡፡ በዚህ ግንኙነት ውስጥ  ንብረት ክፍፍልን በተመለከተ ጥያቄ የሚያቀርበው ወገን በግንኙነት ውስጥ አብሮ መኖር መቻል እንዳለበት ጉባዔው ከተወያየ በኋላ አመልካች የጠየቁት ንብረት የተፈራው ከተጠሪ ጋር እንደ ባልና ሚስት ያላቸው ግንኙነት ከተቋረጠ በኋላ ነው፡፡ በመሆኑም በፍ/ቤቱ የተሰጠው ውሳኔ የአመልካችን እኩልነት መብት እና ፍትህ የማግኘት መብት የሚጥስ ሆኖ ባለመገኘቱ ለፍ/ቤቱ ወሳኔ የሕገ መንግስት ትርጉም አያስፈልገውም በሚል ውሳኔ አሳልፏል፡፡

ሁለተኛው አወያይ ጉዳይ በአመልካችና ተጠሪ መካከል በነበረው የዲስፕሊን ክርክር በሚመለከት “በጉዳዩ ላይ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የሰጠው ውሳኔ ተገቢ ስላልሆነ የሕገ መንግሥት ትርጉም ይሰጥልኝ” በሚል ለአጣሪ ጉባዔው የቀረበ ጉዳይ ነው። ጉባዔውም በጉዳዩ ላይ ሕገ መንግሥቱን እና በአመልካች የቀረቡትን አቤቱታዎች መሰረት በማድረግ ሰፊ ክርክር ካደረገ በኋላ  በአብላጫ ድምፅ በጉዳዩ የሕገ መንግሥታዊ ጥያቄ ያልተገኘበት በመሆኑ የሕገ መንግስት ትርጉም አያስፈልገውም የሚል ውሳኔ አስተላልፏል።

ይህ ጉዳይ ከዚህ ቀደም ጉባዔው ተወያይቶበት በተጠሪ ምላሽ እንዲሰጥበት ያደረና በተጠሪ በኩል ምላሽ የተሰጠበት ጉዳይ ሲሆን፣ ረቡዕ ታህሣስ 26/2015 የመጨረሻ እልባት አግኝቶ መዝገቡ ተዘግቷል።