“እያንዳንዱ ፈፃሚ እና አመራር የሚያስመሰግን ሥራ በመሥራት ተቋማዊ ለውጥ ለማምጣት መሥራት አለበት።” የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ ዋና ዳይሬክተር አቶ ደሳለኝ ወዬሳ።
June 4, 2024
Show all

ጉባዔው በ7 የአቤቱታ መዛግብት ላይ ተወያይቶ ውሳኔ እና አቅጣጫ አስቀመጠ።

የኢፌዴሪ የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ ሐሙስ ግንቦት 29 ቀን 2016 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ በንዑስ አጣሪ ጉባዔ እና በአጣሪ ጉባዔ ጽ/ቤቱ የሕግ ተመራማሪዎች ሰፊ ማጣራት ተደርጎባቸው ለውሳኔ ከቀረቡለት የሕገ መንግሥት የትርጉም አቤቱታዎች መካከል 7 በሚሆኑት ላይ ተወያይቶ ውሳኔ እና አቅጣጫ አስቀምጧል።

ከእነዚህም መካከል ከውክልና ጋር በተያያዘ የንብረት መብተ ላይ አመልካች በሕገ መንግሥቱ አንቀጾች 40፣ 79፣ 80 እና 25 ላይ የተደነገጉ መብቶቼ ተጥሰዋል በማለት ሕገ መንግሥታዊ ጥያቄ ያቀረቡ ሲሆን ጉባዔውም ጉዳዩን ከመረመረ በኋላ ሕገ መንግሥታዊ ጥሰት አልተፈፀመም በሚል እንዲዘጋ ወስኗል።

በሌላ በኩል በንብረት ክርክር ላይ አመልካች ሕገ መንግሥታዊ ፍትሕ የማግኘት እና የንብረት መብቴ ተጥሷል በሚል ላቀረቡት አቤቱታ ተጨማሪ መጣራት ተደርጎበት ለውሳኔ እንዲቀርብ ጉባዔው አቅጣጫ ሰጥቷል።

ከላይ ከተጠቀሱት አቤቱታዎች በተጨማሪ  በንብረት መብት፣ ፍትህ ከማግኘት፣ ከእኩልነት፣ ከዳኝነት ስልጣን፣ እና ከሌሎች ሕገ መንግሥታዊ አቤቱታዎች እንዲሁም የፌዴሬሽን ም/ቤት ከሰጣቸው አስገዳጅ ውሳኔዎች ጋር በተያያዝ የቀረቡለትን 5 የትርጉም አቤቱታዎች በመመርመር በአመልካቾች ምላሽ እንዲሰጥባቸውና ለውሳኔ እንዲቀርቡት ጉባዔው ትዕዛዝ ሰጥቷል።