ጉባዔው በ80 የአቤቱታ መዛግብት ላይ ተወያይቶ ውሳኔ እና አቅጣጫ አስቀመጠ።
June 18, 2024
የመብቶች ጥበቃና ሕገ መንግሥታዊ ክትትል ላይ አለምአቀፍ ውይይት እየተካሄደ ነው
June 27, 2024
Show all

ጉባዔው በ43 የሕገ መንግሥት አቤቱታዎች ላይ ብይን ሰጠ።

????????????????????????????????????

ሰኔ 14 ቀን 2016 ዓ.ም

የኢፌዴሪ የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ ሐሙስ ሰኔ 13 ቀን 2016 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ በንዑስ አጣሪ ጉባዔ እና በአጣሪ ጉባዔ ጽ/ቤቱ የሕግ ተመራማሪዎች ተገቢው ምርመራ እና ማጣራት ተደርጎባቸው ለውሳኔ በቀረቡለት የሕገ መንግሥት የትርጉም አቤቱታዎች ላይ ከተወያዬ በኋላ 43 በሚሆኑት ላይ ውሳኔ፣ የውሳኔ ሐሳብና አቅጣጫ ሰጥቷል።

ጉባዔው በዕለቱ ባደረገው ስብሰባ ከተመለከታቸው 44 የትርጉም አቤቱታዎች ውስጥ 40 የሚሆኑት የሕገ መንግሥት ጥሰት አልተፈፀመባቸውም በሚል የባለጉዳዮችን አቤቱታ ውድቅ በማድረግ እንዲዘጉ ወስኗል።

በሌላ በኩል በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 37 እና 40(4) የተጠበቁልኝ ፍትሕ የማግኘት እና ከገጠር መሬት ይዞታ ያለመፈናቀል መብቶቼ ተጥሰውብኛል በሚል ለጉባዔው በቀረበ አንድ የትርጉም አቤቱታ ላይ ጉባዔው ሰፊ ውይይት በማድረግ ሕገ መንግሥታዊ ጥሰት መፈፀሙን በማመን የመጨረሻ ውሳኔ ይሰጥበት ዘንድ የውሳኔ ሐሳቡ ለፌዴሬሽን ም/ቤት እንዲላክ ወስኗል።

ከዚህ በተጨማሪም በንብረት መብት ላይ በቀረበ የትርጉም አቤቱታ ላይ ውይይት ያደረገው ጉባዔው፤ በጉዳዩ ላይ  ተጨማሪ ማጣራት ተደርጎበት ለውሳኔ እንዲቀርብ ያዘዘ ሲሆን በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 20 ላይ በተደነገገው መሠረት በጠበቃ የመወከል ሕገ መንግሥታዊ መብቴ ተጥሷል በሚል ለቀረበለት ሕገ መንግሥታዊ አቤቱታ ደግሞ በተጠሪ ምላሽ እንዲሰጥበት ትዕዛዝ መስጠቱን ለመረዳት ተችሏል።

አጣሪ ጉባዔው የትርጉም ጥያቄ መኖሩን ያመነበት እንደሆነ በጉዳዩ ላይ የሚሰጠውን ሕገ መንግሥታዊ ትርጉም ለፌዴሬሽኑ ምክር ቤት ለመጨረሻ ውሳኔ እንደሚያቀርብ እና የፌዴሬሽን ምክር ቤትም የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ በሚያቀርብለት ሕገ መንግሥታዊ ጉዳይ ላይ በሠላሳ ቀናት ውስጥ ውሳኔ እንደሚሰጥ በሕገ መንግሥቱ አንቀጾች 83 እና 84 ላይ ተደንግጎ ይገኛል።