ሴንት ፒትርስበርግ በተካሄደው የአለምአቀፍ ስብሰባ ኢትዮጵያ ልምዷን አካፈለች
May 19, 2023
ጉባዔው በባለጉዳይ አቤቱታዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ
May 26, 2023
Show all

ጉባዔው በ11 ሕገ መንግሥታዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ

????????????????????????????????????

የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ ሐሙስ ግንቦት 10 ቀን 2015 ዓ.ም ባደረገው መደበኛ ስብሰባ ቀደም ሲል በዋና እና በንዑስ ጉባዔ ደረጃ ሲወያይባቸው በነበሩ 11 ሕገ መንግሥታዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ስምንቱ ላይ ውሳኔ አሳለፈ፡፡

ጉባዔው ውይይት ካደረገባቸው 11 ጉዳዮች ውስጥ ስምንቱ ላይ ምንም አይነት የሕገ መንግሥት ጥሰት ስላላገኘባቸው የሕገ መንግሥት ትርጉም አያስፈልጋቸውም ብሎ ውሳኔ በማሳለፍ ዘግቷቸዋል፡፡ ሁለት መዝገቦች አንዱ በተጠሪ መልስ እንዲሰጥበት ሌላኛው አስተያየት እንዲሰጥበት ትእዛዝ ሲያስተላልፍ፤ አንድ መዝገብ ደግሞ ተጨማሪ መረጃዎች ተጠናቅረውና አፃፃፉ ተስተካክሎ እንዲመጣ አሳድሮታል፡፡

ጉባዔው ሰፊ ውይይት ካደረገባቸው ጉዳዮች አንዱ በመዝገብ ቁጥር 6582/14 የቀረበው ጋብቻ በፍች ከመፍረስ ጋር ተያይዞ የቀረበ የንብረት ክርክር ነው፡፡ ከጋብቻ በፊት በአንድ ተጋቢ ብቻ የተፈራ ንብረት በጋብቻ ውስጥ ማሻሻያ ሲደረግበት ቆይቶ ከፍች በኋላ ንብረቱ እንዴት ሊካፈል ይችላል በሚለው ላይ የፍ/ቤቱን ውሳኔ ከሕገ መንግሥቱ አንፃር በመመርመር ጉባዔው ሰፊ ውይይት ካደረገ በኋላ ለውሳኔ አሰጣጥ እንዲያመች ተጠሪ መልስ እንዲሰጥበት ትእዛዝ አስተላልፏል፡፡

በጉባዔው ሰፊ ውይይት የተደረገበት ሌላው ጉዳይ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ማህበራዊ ፍ/ቤት አመልካችነት በመዝገብ ቁጥር 3670/10/15 የሕግ ሕገ መንግሥታዊነት ላይ የቀረበ የሕገ መንግሥት ትርጉም ጥያቄ ሲሆን ጉባዔው ከሕገ መንግሥቱ አንቀፅ 9 እና 13 አንዲሁም  ከሕገ መንግሥቱ አንቀፅ  20፣ 37፣ እና 78(4) አንፃር ሰፊ ውይይት አድርጎ ደንቡን ያወጣው የመንግሥት አካል የተጠቀሱትን የሕገ መንግሥቱ አንቀፆች መሰረት በማድረግ በጉዳዩ ላይ አስተያየት እንዲሰጥበት አቅጣጫ አስቀምጦ ስብሰባውን አጠናቋል፡፡