የሀዘን መግለጫ:-በሕገ መንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ አባልነት ለረዥም ጊዜ በትጋት እያገለግሉ የነበሩት ክቡር አቶ ክፍለፅዮን ማሞ ባደረባቸው ድንገተኛ ህመም በዛሬው እለት ከዚህ አለም በሞት…
November 11, 2020
የጉባዔው ጽ/ቤት አመራርና ሠራተኞች የፀረ ሙስና ቀንን አከበሩ
December 5, 2020

ጉባዔው በአንድ ሕገ መንግስታዊ ጉዳይ ላይ የውሳኔ ሀሳብ አሳለፈ

ጉባዔው በአንድ ሕገ መንግስታዊ ጉዳይ ላይ የውሳኔ ሀሳብ አሳለፈ

 

የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ ዛሬ ህዳር 17/2013 ዓ.ም ባካሄደው ስብሰባ ሰላሳ አምስት ጉዳዮችን በማጣራት ሰለላሳ ሁለቱን ጉዳዮች የሕገ መንግስት ትርጉም አያስፈልጋቸውም ብሎ ውሳኔ በመስጠት የዘጋቸው ሲሆን ሁለት ጉዳዮችን ለተጨማሪ ምርመራ አሳድሯቸዋል፡፡ በአንድ  ጉዳይ ላይ ደግሞ የውሳኔ ሀሳብ በማሳለፍ ለመጨረሻ ውሳኔ ወደ ፌዴሬሽን ምክር ቤት እንዲላክ ወስኗል፡፡

 

ጉባዔው ስብሰባውን ከመጀመሩ በፊት የጉባኤው አባል የነበሩትንና በቅርቡ በሞት የተለዩትን ክቡር አቶ ክፍለፅዮን ማሞን  በህሊና ፀሎት አስቧል፡፡ በዛሬው ውሎ ከመረመራቸው ሰላሳ አምስት ጉዳዮች ውስጥ የውሳኔ ሀሳብ የቀረበት ጉዳይ በመዝገብ ቁጥር 2165/09 የተቀመጠውና አመልካች አለአግባብ የተያዘብኝ ደመወዝ ይከፈለኝ በሚል የቀረበው ክርክር ሲሆን፤ ጉዳዩ በየኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ ውሳኔ ያገኘና ክሱ በቀረበበት ሀገረ ስብከት ያልተፈፀመ የገንዘብ ጉዳይ እንጂ ሀይማኖታዊ ጉዳይ አለመሆኑ እየታወቀ የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በመ.ቁ.119978 ጉዳዩን ተቀብሎ አለማስተናገዱና የሃይማኖት ጉዳይ ስለሆነ ጉዳዩን የማየት ስልጣን የለኝም በማለት የሰጠው ውሳኔ  የአመልካችን ንብረት የማፍራትና ፍትህ የማግኘት ሕገ መንግስታዊ መብት የሚጥስ ስለሆነ ለመጨረሻ የሕገ መንግስት ትርጉም ወደ ፌዴሬሽን ም/ቤት እንዲላክ ወስኗል፡፡