ጉባዔው በአንድ ሕገ መንግስታዊ ጉዳይ ላይ የውሳኔ ሀሳብ አሳለፈ
February 1, 2021
ጉባዔው በሁለት ሕገ መንግሥታዊ ጉዳዮች ላይ የውሳኔ ሀሳብ አሳለፈ
March 4, 2021

ጉባዔው በአንድ ሕገ መንግስታዊ ጉዳይ ላይ የውሳኔ ሀሳብ አሳለፈ

ጉባዔው በአንድ ሕገ መንግስታዊ ጉዳይ ላይ የውሳኔ ሀሳብ አሳለፈ

 

የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ የካቲት 3 ቀን 2013 ዓ.ም ባካሄደው ስብሰባ ሀያ ስድስት ጉዳዮች ላይ በመወያት ሀያ አራት ጉዳዮችን የሕገ መንግስት ትርጉም አያስፈልጋቸውም ብሎ ውሳኔ በመስጠት የዘጋቸው ሲሆን  አንድ ጉዳይ ለተጨማሪ ምርመራ አሳድሮታል፡፡ በአንድ  ጉዳይ ላይ ደግሞ የውሳኔ ሀሳብ በማሳለፍ ለመጨረሻ ውሳኔ ወደ ፌዴሬሽን ምክር ቤት እንዲላክ ወስኗል፡፡

 

ጉባዔው በዛሬው ውሎ ከመረመራቸው ሀያ ስድስት ጉዳዮች ውስጥ የውሳኔ ሀሳብ የቀረበት ጉዳይ በመዝገብ ቁጥር 2482/09 የተቀመጠና አመልካች በየደረጃው ባሉ ፍ/ቤቶች ውሳኔ የእርሻ መሬታቸውንና በመሬቱ ላይ ያሉ ቋሚ ንብረታቸውን ለሀይማኖት ተቋም አለአግባብ እንዲለቁ የተወሰነውን ውሳኔ በመቃወም የቀረበ ክርክርን የሚመለከት ነው፡፡

ጉዳዩ አመልካች ክርክር የተደረገበትን 1.20 ሄክታር የእርሻ መሬት ይዞታ በኦሮምያ ከልል የሌሙና ቢልቢሎ ወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤት፣ የወረዳው የመሬት አስተዳደር እና አካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት በ235 ሺ ብር ካሳ ካለፈቃዳቸው መሬታቸውንና በመሬቱ ላይ ያሉ ቋሚ ንብረታቸውን ሙሉ ለሙሉ ለሀይማኖት ተቋም እንዲለቁ ማስገደዳቸው አንደኛ በሕገ መንግሥቱ አንቀፅ  40(4)  መሰረት ከመሬት ያለመነቀል መብታቸውን የሚጥስ ስለሆነ፣ ሁለተኛ የኦሮምያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ጥያቄው ለቅሬታ ሰሚ ኮሚቴው ባለመቅረቡ ጉዳዩን  የማየት ስልጣን የለኝም ብሎ የአመልካችን ቅሬታ በመደበኛ ፍ/ቤት እንዳይታይ መወሰኑና የፌደራል ሰበር ሰሚ ችሎቱም ማፅናቱ በሕገ መንግስቱ አንቀፅ 37 የተቀመጠውን የአመልካችን ፍትህ የማግኘት መብት የሚጥስ በመሆኑ ለመጨረሻ የሕገ መንግስት ትርጉም ወደ ፌዴሬሽን ም/ቤት እንዲላክ የውሳኔ ሀሳቡን አቅርቧል፡፡