የሕገ መንግሥት አተረጓጎምና የውሳኔ አፈፃፀም ችግሮችን ለመፍታት ሁሉም አካል የራሱን ሀላፊነት መወጣት እንዳለበት ተጠቆመ
February 1, 2021
ጉባዔው በአንድ ሕገ መንግስታዊ ጉዳይ ላይ የውሳኔ ሀሳብ አሳለፈ
February 17, 2021

ጉባዔው በአንድ ሕገ መንግስታዊ ጉዳይ ላይ የውሳኔ ሀሳብ አሳለፈ

ጉባዔው በአንድ ሕገ መንግስታዊ ጉዳይ ላይ የውሳኔ ሀሳብ አሳለፈ

 

የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ ጥር 19 ቀን 2013 ዓ.ም ባካሄደው ስብሰባ ሶስት ጉዳዮች ላይ በስፋት በመወያት አንድ ጉዳይ የሕገ መንግስት ትርጉም አያስፈልገውም ብሎ ውሳኔ በመስጠት የዘጋው ሲሆን  ሌላውን አንድ ጉዳይ ለተጨማሪ ምርመራ አሳድሮታል፡፡ በአንድ  ጉዳይ ላይ ደግሞ የውሳኔ ሀሳብ በማሳለፍ ለመጨረሻ ውሳኔ ወደ ፌዴሬሽን ምክር ቤት እንዲላክ ወስኗል፡፡

 

ጉባዔው በዛሬው ውሎ ከመረመራቸው ሶስት ጉዳዮች ውስጥ የውሳኔ ሀሳብ የቀረበት ጉዳይ በመዝገብ ቁጥር 2291/09 የተቀመጠና በአመልካቾችና በመንግስት ቤቶች ኤጀንሲ መካከል ያለ የቤት ክርክርን የሚመለከት ነው፡፡

ጉዳዩ መልካቾች ክርክር የተደረገበትን ቤት ከ1970ዓ.ም ጀምሮ በእጃቸው አድርገው እየተጠቀሙበት እንደሚገኙ በተጠሪም እየታመነ ቤቱን በመንግስት እጅ እንደሚገኝ ቤት ተቆጥሮ የፌደራል ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ.ቁ 14094 የሰጠውን የህግ ትርጉም እንደማጣቀሻ በመጠቀም የሰጠው ውሳኔ ማለትም “… አንድ ለረጅም አመታት በመንግስት እጅ የነበረን ቤት ይገባኛል የሚል ጠያቂ ቤቱ በአዋጅ 47/67 የተፈቀደለት ወይም ደግሞ ያላግባብ ከአዋጅ ውጪ ተወስዶብኛል የሚሉም ከሆነ ለሚመለከተው አካል ጥያቄያቸውን አቅርበው ውሳኔ አግኝተው ባለመብት ስለመሆናቸው ሊያስረዱ ይገባል …”የሚለውን በመጥቀስ በሕግ ከተቀመጠው አሰራር ውጭ ሌላ ግምት በመውሰድ ቤቱን እንዲለቁ መወሰኑ፤ እንዲሁም  የቤቱ ባለቤትነት በህገ ወጥ መንገድ ከተጠሪ እጅ ወጥቷል ለሚለው በህግ አግባብ ማስረጃ አቅርቦ ባላረጋገጠበት ሁኔታ ፍ/ቤቱ የማስረዳት ሽክሙን ወደ አመልካቾች በማዞር መብታቸውን ማሳጣቱ  በሕገ መንግስቱ አንቀፅ 40(1)፣ 25 እና 79(3) የተቀመጠውን የአመልካችን ንብረት የማፍራትና የመጠቀም፣  የሕግ ዋስትና የማግኘት መብት እንዲሁም ዳኞች ከሕግ በስተቀር በሌላ ሁኔታ አይመሩም የሚለውን ሕገ መንግስታዊ መብት የሚጥስ ስለሆነ ለመጨረሻ የሕገ መንግስት ትርጉም ወደ ፌዴሬሽን ም/ቤት እንዲላክ የውሳኔ ሀሳቡን አቅርቧል፡፡