ጉባዔው በሁለት የአቤቱታ መዛግብት ላይ የሕገ መንግሥት ትርጉም ያስፈልጋቸዋል በማለት ውሳኔ አሳለፈ።
November 10, 2023
የአዋጅ ቁጥር 47/67 ክርክሮችና ሕገ መንግሥታዊነታቸው
November 21, 2023
Show all

ጉባዔው በስድስት የአቤቱታ መዛግብት ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ።

????????????????????????????????????

ኅዳር 7 ቀን 2016 ዓ.ም (አዲስ አበባ)

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ ህዳር 6 ቀን 2016 ዓ.ም ባደረገው መደበኛ ጉባዔ በንዑስ አጣሪ ጉባዔ እና በባለሙያዎች ጥናት እና ማጣራት ሲደረግባቸው በቆዩ ስድስት የሕገ መንግሥት ትርጉም አቤቱታዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ ሰጥቷል።

በዚህም በዕለቱ ከቀረቡት አቤቱታዎች መካከል በመዝገብ ቁጥር  8039/15 እና በመዝገብ ቁጥር 4487/11 የተጠቀሱት ሁለት አቤቱታዎች የሕገ መንግሥት ጥሰት የለባቸውም በሚል እንዲዘጉ የወሰነ ሲሆን አንድ  የአቤቱታ መዝገብ ላይ ደግሞ ተጨማሪ ማጣራት ተደርጎበት ድጋሚ እንዲቀርብ በይደር ታልፏል።

በሌላ በኩል በሦስት የትርጉም አቤቱታዎች ላይ ጉባዔው በስፋት ከተወያየባቸው በኋላ በተጠሪ  መልስ እንዲሰጥባቸው ጉባዔው ውሳኔ ሰጥቷል።

እነዚህ መልስ እንዲሰጥባቸው የተወሰነባቸው ሦስት አቤቱታዎችም የቤት ክርክር፣ የደንብ ቁጥር 54/2005 አንቀፅ 17 እና 19 ሕገ መንግሥታዊነት ክርክር እንዲሁም የኪራይ እና ሽያጭ ውል ክርክርን የሚለከቱ አቤቱታዎች ናቸው።