የሕገ መንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ ጽ/ቤት ሰራተኞች የሰንደቅ አላማ ቀንን በደማቅ ሁኔታ አከበሩ
October 16, 2018
November 1, 2018

ጉባዔው በሁለት ጉዳዮች ላይ የሕገ መንግሥት ትርጉም እንዲሰጥባቸው ለፌ/ም/ቤት የውሳኔ ሃሳብ አቀረበ

የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ ጥቅምት 14 ቀን 2011 ዓ.ም ለግማሽ ቀን ባካሄደው ጉባዔ የስምንት አቤቱታ አቅራቢዎችን መዝገብ በመመርመር በሁለቱ ላይ የሕገ መንግሥት ትርጉም የውሳኔ ሃሳብ ያቀረበ ሲሆን፣ ሦስቱን ትርጉም አያስፈልጋቸውም በማለት ውሳኔ ሰጥቶ ሲዘጋ ቀሪ ሦስት መዝገቦች ላይ ደግሞ የተለያዩ ሀሳቦች ከተንሸራሸሩና ክርከሮች ከተደረገባቸው በኋላ ተጨማሪ ማጣራት እንዲደረግባቸው በይደር አልፏቸዋል።

ለሕገ መንግሥት ትርጉም ወደ ፌዴሬሽን ምክር ቤት የውሳኔ ሃሳብ ከቀረበባቸው ሁለት መዝገቦች መካከል የመጀመሪያው መዝገብ በሕገ መንግሥቱ የተደነገጉ ሁለት መብቶችን ማለትም በአንቀፅ 37/1 የተደነገገውን ፍትህ የማግኘት መብትን እንዲሁም አንቀፅ 40/1 ላይ የሰፈረውን የንብረት መብት ጥሶ የተገኘ ነው በማለት ሲሆን፣ ሁለተኛው መዝገብ ደግሞ በአንቀፅ 40/3 ላይ የተደነገገውን ከመሬት ይዞታ ያለመፈናቀል መብትን ጥሶ የተገኘ በመሆኑ ነው። ጉባዔው በይደር ያለፋቸውን መዝገቦች ጨምሮ ሌሎች መዝገቦችን በቀጣዩ ጉባዔ ለማየት ቀጠሮ ይዟል።