ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት የአፍሪካ ሕገ መንግሥታዊ ፍ/ቤት ዋና ፀሐፊን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ።
March 27, 2024
የጉባዔ ጽ/ቤቱ አመራሮችና ሠራተኞች የሴቶችን ቀን አከበሩ።
March 27, 2024
Show all

ጉባዔው ሦስተኛውን የመሰማት መድረክ አካሄደ።

የኢፌዴሪ የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ በታሪኩ ሦስተኛውን የመሰማት መድረክ የካቲት 30 ቀን 2016 ዓ.ም አድርጓል። በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት እና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሚኖሩ ነዋሪዎች መካከል በሚነሱ የፍትሃብሔር ክርክሮች እንዲሁም የአደገኛ ቦዘኔነት መቆጣጠሪያ አዋጅ ቁጥር 384/96 አንቀፅ 4 እና 6ን በሚመለከት በቀረቡ የሕገ መንግሥት የትርጉም አቤቱታዎች ላይ የሚመለከታቸውን አካላት አስተያዬት የመስማት መድረክ (Public Hearing) አካሄደ።በሁለቱ ርዕሰ ጉዳዮች ላይም ከተለያዩ የዘርፉ የሙያ ማኅበራት፣ ከትምህርት ተቋማት፣ ከሰብአዊ መብት ኮሚሽን እና ከፌደራልና ከክልል የፍትህ ተቋማት የተወከሉ የሕግ ባለሙያዎች በመገኘት ቀደም ሲል በፅሁፍ ያቀረቡትን ሙያዊ አስተያት መሰረት በማድረግ በግል እና በቡድን ያላቸውን ሙያዊ አስተያዬት አንፀባርቀዋል፤ ከጉባዔው ለቀረበላቸው ጥያቄዎችም ማብራርያ ሰጥተዋል።በነበረው የሙያ አስተያዬት የመሰማት መድረክ ላይ ተገኝተው ሐሳብና አስተያዬታቸውን ለሰጡ አካላት ምስጋና ያቀረቡት የኢፌዴሪ የሕገ መንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ ሰብሳቢ እና የፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት፤ ለሕግ የበላይነት መስፈን እና ለሕገ መንግሥታዊነት እንዲሁም ለሕግ ዕውቀት መዳበር ተሳታፊዎቹ ላበረከቱት አስተዋፅኦ ከፍተኛ አክብሮት እንዳላቸው የገለፁ ሲሆን ቀጣይ በሚኖሩ ተመሳሳይ መድረኮች ላይም መሰል ሐሳብና አስተያዬታቸውን መስጠት እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል።