በኢትዮጵያ ፍደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ የህገመንግሰት አጣሪ ጉባዔ ለመላው ኢትዮጵያውያን ዲሱ አመት 2012 የሰላም፡የፍቅር፡የአንድነት፡የትብብር፡የእድገት እና የብልጽግና እንዲሆን ይመኛል
September 17, 2019
የሕገ መንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ ጽ/ቤት ለፌደሬሽን ምክር ቤት አባላት ስልጠና ሰጠ
October 10, 2019

ጉባዔው መስከረም 21/2012 ዓ.ም ባደረገው ጉባዔ ሁለት ጉዳዮች የሕገ መንግሥት ትርጉም እንዲሰጥባቸው ለፌ/ም/ቤት የውሳኔ ሃሳብ አቀረበ

ጉባዔው መስከረም 21/2012 ዓ.ም ባደረገው ጉባዔ ሁለት ጉዳዮች የሕገ መንግሥት ትርጉም እንዲሰጥባቸው ለፌ/ም/ቤት የውሳኔ ሃሳብ አቀረበ

የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ መስከረም 21 ቀን 2012 ዓ.ም ለግማሽ ቀን ባካሄደው ጉባዔ የአቤቱታ አቅራቢዎችን መዝገብ በመመርመር በሁለቱ ላይ የሕገ መንግሥት ትርጉም ያስፈልጋቸዋል በማለት የውሳኔ ሃሳብ ለፌዴሬሽን ም/ቤት ያቀረበ ሲሆን፣ ሶስት ጉዳዮችን ትርጉም አያስፈልጋቸውም በማለት ውሳኔ ሰጥቶ ዘግቷል።

ለሕገ መንግሥት ትርጉም ወደ ፌዴሬሽን ምክር ቤት የውሳኔ ሃሳብ ከቀረበባቸው ሁለት መዝገቦች መካከል የመጀመሪያው በመዝገብ ቁጥር 1674 የተመዘገበና በሕገ መንግሥቱ አንቀፅ 37 የተደነገገውን ፍትህ የማግኘት መብትን ጥሶ በመገኘቱ ሲሆን፣ ሁለተኛው መዝገብ ደግሞ በአንቀፅ 79/3 ላይ የተደነገገውን ዳኞች ከህግ በስተቀር በሌላ ሁኔታ አይመሩም የሚለውን የመንግስቱን ድንጋጌ ፍርድ ቤቱ በውሳኔው በመተላለፍ ጥሶ የተገኘ በመሆኑ ነው። ጉባዔው ሌሎች መዝገቦችን በቀጣዩ ጉባዔ ለማየት ቀጠሮ ይዟል።