“አሁን ያለንበትን ወቅት የሕገ መንግሥት ጊዜ በማለት ልንጠራው እንችላለን” ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ
May 20, 2020
በሕገ መንግስት ትርጉም ጥያቄ ላይ የባለሙያዎች ሃሳብ
May 21, 2020

ጉባዔው ሕገ መንግሥቱ ሲረቅና ሲፀድቅ ተሳትፈው የነበሩ አካላትን አስተያየት አዳመጠ

ጉባዔው ሕገ መንግሥቱ ሲረቅና ሲፀድቅ ተሳትፈው የነበሩ አካላትን አስተያየት አዳመጠ
የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ ሕገ መንግሥቱ ሲረቅና ሲፀድቅ በአርቃቂነት፣ በአፅዳቂነትና በሙያቸው ተሳትፎ ያደረጉ አካላትን ግንቦት 10/2012 በሸራተን አዲስ ሆቴል በተደረገው አስተያየት የማድመጥ (Hearing) ስነ ሥርዓት ሀሳባቸውን አዳመጠ።
አስተያየት በማድመጥ (Hearing) ስነ ሥርዓቱ ላይ ከ25 ዓመታት በፊት የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሕገ መንግሥት ሲረቅ ተሳትፎ የነበራቸውን አካላት ሀገር ውስጥ ያሉት እዛው በፕሮግራሙ በመገኘት፣ ያልተገኙት ደግሞ በቀጥታ በስካይፕ አስተያየት እንዲሰጡ ተደርጓል።
አስተያየታቸውን በስካይፕ ከሰጡት ውስጥ ሕገ መንግሥቱ በረቀቀበት ወቅት የሙያ ተሳትፎ ካደረጉት መካከል ፕሮፌሰር እንድርያስ እሸቴ አንዱ ሲሆኑ፣ የሕገ መንግሥት አርቃቂ ኮሚሽን አባል ከነበሩት መካከል አምባሳደር አብዱልአዚዝ አህመድ እና አምባሳደር ታዬ አፅቀሥላሴ ይገኙበታል፡፡ የሕገ መንግሥት አፅዳቂ ጉባዔ አባል ከነበሩት መካከል ደግሞ ዶ/ር ተሰማ ጋዲሳ እና አምባሳደር ተስፋዬ ሀቢሶ በውይይቱ ላይ በአካል በመገኘት በወቅቱ ሕገ መንግሥቱ ሲረቅና ሲፅድቅ የነበረውን ዐውድ በተመለከተ የነበረውን ተጨባጭ ሁኔታ አስረድተዋል፡፡
በተጨማሪም ግንቦት 08/2012 በነበረው የመጀመሪያ ቀን አስተያየት የማድመጥ (Hearing) ስነ ሥርዓት ላይ ያልተገኙ የነበሩት የፖለቲካል ሳይንስና የሕግ ምሁሩ ፕሮፌሰር አለማየሁ ገ/ማርያም በቀጥታ ከካሊፎርኒያ በስካይፕ በመሳተፍ የአሜሪካንን እና የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሕገ መንግሥትን በማጣቀስ ያላቸውን ተሞክሮ ለጉባዔው አቅርበዋል፡፡ በዓለም አቀፍ ተቋም ውስጥ በሰብዓዊ መብት ላይ የሚሠሩት የፒ ኤች ዲ ዕጩ ተመራቂዋ ወ/ሮ መስከረም ገስጥ እንዲሁም በተመሳሳይ የፒ ኤች ዲ ዕጩ ተመራቂ የሆኑት ጠበቃና መምህር አቶ ቸርነት ሆርዶፋ በጉዳዩ ላይ ያላቸውን አስተያየትና ተሞክሮ አቅርበዋል፡፡
ከጉባዔ አባላትም የተለያዩ ጥያቄዎች ተነስተውላቸው ተጨማሪ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ ፕሮግራሙን በቀጥታ ስርጭት ሕዝብ የተከታተለው ሲሆን፣ ጉባዔው የፊታችን ሐሙስ ግንቦት 13/2012 ከዚሁ ከምርጫ መራዘም ጋር በተያያዘ አስተያየት የማድመጥ ስነ ሥርዓቱን ከኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴርና ከምርጫ ቦርድ ጋር የሚቀጥል ይሆናል፡፡