የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ ጽ/ቤት አመራርና ሠራተኞች የ3ተኛውን ዙር የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር አከናወኑ
July 27, 2021
አጣሪ ጉባዔው የ2013 በጀት የስራ አፈፃፀሙን 30 በመቶ ማሳደጉ ተገለፀ
August 17, 2021

የጽ/ቤቱ ሠራተኞች ለሕልውና ዘመቻው የሚጠበቅባቸውን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁነታቸውን ገለጹ

????????????????????????????????????

 

  • የደመወዝና የደም ልገሣ ድጋፍ አደረጉ

የሕገ መንግሥት ጉዳች አጣሪ ጉባዔ ጽ/ቤት ሠራተኞች የአገር ሕልውናን ለማስጠበቅ እየተፋለመ ካለው የአገር መከላከያ ሠራዊት ጎን በመሆን የሚጠበቅባቸውን አገራዊ ኃላፊነት ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን አረጋገጡ፡፡

በወቅታዊ አገራዊ ጉዳይና ወራሪውን የትሕነግ ኃይል ለመመከት እየተካሄደ ባለው የሕልውና ዘመቻ ዙሪያ ውይይት ያካሄዱት የጽ/ቤቱ ሠራተኞች በአገር ሕልውና ላይ የተቃጣውን ወረራ ለመመከት የገንዘብ፣ የደም ልገሣ፣ የጉልበትና የዓይነት ድጋፍን ጨምሮ በዘመቻው እስከመሳተፍ አስተዋጽዖ ለማድረግ ቁርጠኛ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

በዚህም መሠረት ሙሉ የወር ደመወዛቸውን ለመስጠት የወሰኑ ሲሆን፣ ደም በመለገሥም ድጋፋቸውን ገልጸዋል፡፡

ውይይቱን የመሩት የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ ደሣለኝ ወዬሳ የተቃጣብን ወረራ በውጪ ኃይሎች ጭምር የሚደገፍ በመሆኑ ችግሩን ከጦርነትም በላይ የአገር ሕልውናን የሚመለከት አድርገን መመልከት እንዳለብን ጠቁመው፣ በሁሉም መስክ አገራዊ አንድነታችንን አጠናክረን አስፈላጊውን ምላሽ ለመስጠት መረባረብ አለብን ብለዋል፡፡

በውይይቱ ወቅት አስተያየት የሰጡት የጽ/ቤቱ ሠራተኞች በበኩላቸው በአገር ደኅንነትና በሕዝባችን ሕይወት ላይ የተደቀነውን አደጋ ለመመከት መንግሥት እየወሰደ ያለውን የመከላከል ርምጃ ሙሉ በሙሉ እንደሚደግፉ ገልጸው፣ ጉዳዩ አገርን የማዳን ጥሪ በመሆኑ የብሔር፣ የኃይማኖትና የፖለቲካ አመለካከት ልዩነት መፍጠር ሳያስፈልግ ሁሉም ዜጋ በአንድነት ሊሳተፍ እንደሚገባ አመልክተዋል፡፡

በግንባር ተሰልፈው የሕይወት መስዋዕትነት እየከፈሉ ላሉት የአገር መከላከያ ሠራዊትና ለክልል ልዩ ኃይሎች የሚደረገው ድጋፍ መጠናከር እንዳለበት የጠቆሙት አስተያየት ሰጪዎቹ፣ ሠርቶ መጠቀምም ሆነ ወጥቶ መግባት የሚቻለው የአገር ሕልውና ሲከበር በመሆኑ የሚጠበቅባቸውን ማናቸውንም ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን አስታውቀዋል፡፡

የትሕነግ ወረራና የሽብር ተግባር ወገናችን በሆነው የትግራይ ሕዝብ ላይ ጭምር እያደረሰ ያለውን አስከፊ ጉዳት እንደሚገነዘቡና የሽብር ቡድኑ የትግራይን ሕዝብ ፈጽሞ እንደማይወክልም ያላቸውን ዕምነት ገልጸዋል፡፡

የደም ልገሣ መርኃ ግብሩ የተከናወነው ከፌዴሬሽን ምክር ቤት ጽ/ቤት ሠራተኞች ጋር በጋራ ሲሆን፣ በዚሁ ወቅት ለጋዜጠኞች አስተያየት የሰጡት ደም ለጋሾች እንደገለጹት፣ የደመወዝ ድጋፉም ሆነ የደም ልገሣው ለአገር ሕልውና ሊከፈል ከሚገባው ዋጋ አኳያ ትልቅ አስተዋጽዖ ባለመሆኑ በቀጣይነትም ለዘመቻው የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው ለመቀጠል ዝግጁ ናቸው፡፡