የግዥ፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ተግባርና ኃላፊነት

 

የግዥ አገልግሎት

 • የግዥ ፍላጎት በማሰባሰብ የግዥ ዕቅድ ማዘጋጀት፣ በተለያዩ ግዥ ዘዴዎች ግዥ መፈጸም እናንብረቶችን ገቢ ማድረግ፡፡

የንብረት አስተዳደር አገልግሎት

 • ተገዝተው የቀረቡ ንብረቶችን በተጠየቀው መስፈርት መሰረት አረጋግጦ መረከብና መመዝገብ፣ ለጠያቂው አካል በተፈቀደው መሰረት ወጪ ማድረግ፣
 • በዕቃ ግምጃ ቤት የሚገኙ አላቂ ዕቃዎች ወጪና ገቢ ሚዛን መስራት፣ የሚወገዱ ንብረቶችን መለየትና ዓመታዊ የንብረት ቆጠራ እንዲከናወን ማድረግ፡፡

 

የፋይናንስ አገልግሎት

 • በተፈቀደውና በመመሪያው መሰረት አረጋግጦ ክፍያ መፈጸም፣
 • የፋይናንስ መረጃዎችንና ክንውኖችን በIBEX/IFMIS መመዝገብ፣
 • የታክስ ተቀናሾችን መለየት፣ መመዝገብና ለገቢዎች ሚ/ር ገቢ ማድረግ፣
 • ወርሃዊ የሰራ ማስኬጃ ከገ/ሚር መጠየቅ፣
 • ፔሮል ማዘጋጀት፣ የባንክ ስቴትመንት ማምጣት፣ የባንክ ሂሳብ ማስታረቂያና ሂሳብ መግለጫዎች ማዘጋጀት፣
 • ወርሃዊ የጥሬ ገንዘብ ቆጠራ ማስደረግ፣ ዓመታዊ የፋይናንስ ኦዲት ማስደረግ
 • በሚሰጠው የኦዲት ግብረ-መልስ መሰረት የማስተካከያ እርምጃ መውሰድና የመዝጊያ ሂሳብ (ክሎዚንግ ባነስ መግለጫ ማዘጋጀት)፡፡

የስምሪት አገልግሎት

 • በኪ.ሜትርና በኮታ መሰረት የነዳጅና ቅባት ዕደላ ማከናወን፣
 • ተሸከርካሪዎች ንጽህናቸውን እንዲጠበቅ መከታተል፣
 • ተሽከርካሪዎች በየሳምንቱ ከስራ ውጪ እንዳይንቀሳቀሱ ኪ.ሜ ምዝገባና ቁጥጥር ማካሄድ፣
 • ተሽከርካሪዎች ብልሽት ሲያጋጥማቸው ጥገና እንዲደረግላቸው ማድረግ፣
 • ግጭት የደረሰባቸው ተሸከርካሪዎች ኢንሹራንስ ክሌም መሙላትና ጥገናውን መከታተል፣
 • ለተሸከርካሪዎች ኣመታዊ ምርመራ ክላውዶና የመድን ዋስትና እድሳት ማድረግ፣
 • ተሸከርካሪዎች አጠቃላይ የኢንሹራንስ አገልግሎት ወቅቱን ጠብቆ እንዲገኙ ማድረግ፡፡

ጥገና አገልግሎት

 • የውስጥ ኤሌክትሪክ መስመር መዘርጋት፣ ብልሽት ሲያጋጥም መጠገን፣
 • በመታጠቢያ ቤቶችና በቢሮዎች አካባቢ ውሃ ቧንቧ ብልሽት መጠገን፣
 • በቢሮዎች አካባቢ በሮች፣ መስኮቶችና የቢሮ መገልገያ ዕቃዎችን መጠገን፡፡

የቢሮ ውበት /ጽዳት/ አገልግሎት

 • አዳራሾችን፣ ቢሮዎችን፣ ደረጃዎችን፣ ኮሪደሮችንና መጸዳጃ ቤቶችንና የቢሮ መገልገያዎችን ማጽዳት፣መጋረጃዎችንና ምንጣፎችን ማጠብ፣
 • ጽዳት በሚከናወንበት ወቅት የቢሮና የንብረቶችን ደህንነትን መጠበቅ፡፡

የጥበቃ አገልግሎት

 • የጥበቃ አገልግሎቱ በአግባቡ መከናወኑን መከታተል

የዕቅድ ዝግጅት፣ ክትትልና ግምገማ አገልግሎት

 • የአጭር፣ የመካከለኛና የረጅም ጊዜ ዕቅድና ለዕቅድ ማስፈጸሚያ በጀት ማዘጋጀት፣
 • የፕሮጀክቶች ፕሮፖዛል ማዘጋጀት፣ አፈጻጸም መከታተልና መደገፍ፣
 • የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ማዘጋጀትና ለሚመለከታቸው አካላት እንዲደርሳቸው ማድረግ
 • ክትትልና ድጋፍ በማድረግ ክፍተቶችን መለየት፣የመፍትሄ ሃሳብ ማቅረብ፣