ጉባዔው ሦስተኛውን የመሰማት መድረክ አካሄደ።
March 27, 2024
አጣሪ ጉባዔው በየጊዜው የተሻለ ሥራ እየሠራ መሆኑን ዕውቅና መስጠት እፈልጋለሁ ሲሉ የፌዴሬሽን ም/ቤት አፈ ጉባዔ የተከበሩ አቶ አገኘሁ ተሻገር ተናገሩ።
March 27, 2024
Show all

የጉባዔ ጽ/ቤቱ አመራሮችና ሠራተኞች የሴቶችን ቀን አከበሩ።

መጋቢት 2 ቀን 2016 ዓ.ም (አዲስ አበባ)የኢፌዴሪ የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ ጽ/ቤት አመራሮችና ሠራተኞች በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ113ኛ እንዲሁም በሀገራችን ደረኛ ለ48ኛ ጊዜ እየታሰበ የሚገኘውን ዓለም አቀፍ የሴቶችን ቀን አከበሩ።በመድረኩ ላይ ንግግር ያደረጉት በአጣሪ ጉባዔ ጽ/ቤቱ የጥናትና ምርምር ቡድን መሪ የሆኑት ወ/ሮ ራሔል ብርሃኑ እንደተናገሩት ሴቶችን በኢኮኖሚያዊ፣ በማኅበራዊ እና በፖለቲካዊ መስኩ ማብቃት፣ ያላቸውን አቅም እንዲጠቀሙ ዕድሉን መስጠት እና መደገፍ አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል። ወ/ሮ ራሔል አክለውም የሴቶች ቀን የሚከበርበት ምክንያት ፆታዊ መድሎን ለማስቀረት እና የሥርዓተ ፆታ እኩልነትን ለማረጋገጥ፣ ሴቶችን ለማበረታታት፣ ሕብረተሰቡ ከፆታዊ መድሎ እንዲፀዳ ለማስተማርና በዚህ ጉዳይ ላይ የተሠሩ ሥራዎችን ለመገምገም መሆኑን አስረድተዋል።በውይይቱ ላይ የታደሙ የጽ/ቤቱ አመራሮችና ሠራተኞችም አጣሪ ጉባዔ ጽ/ቤቱ ለሴቶች ልዩ ትኩረት በመስጠት እንዲሁም ሴቶች በልዩነት ያለባቸውን ቤተሰብ የመምራት እና የማስተዳደር ጫና በመረዳት ለሚጠይቋቸው ጥያቄዎች ምላሽ እና መፍትሄ መስጠት እንደሚገባ ተናግረዋል። በሌላ በኩል ሴቶችን በአመራርነት፣ በደሞዝ እና ጥቅማ ጥቅም በትምህርት እና ስልጠና፣ በሕፃናት ማቆያ እና መሰል ሴቶችን በልዩነት በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ ልዩ ትኩረት እንደሚሻ ከመድረኩ ተነስቷል።የሴቶችን ተግዳሮት መፍታት ሴቶችን ለማብቃት ወሳኝ ነው ያሉት ወ/ሮ ራሔል፤ የሴቶችን ጥቅም በማስከበር በኩል በአጣሪ ጉባዔ ጽ/ቤቱ በኩል ጅምሮች እንዳሉ ነገር ግን እንደ ተቋም ብዙ ነገር መሥራት እና ለሌሎች ተቋማት አርዓያ መሆን እንደሚገባም አመላክተዋል።በሀገራችን ኢትዮጵያ ወደ 52% የሚሆኑት የማሕበረሰባችን ክፍሎች ሴቶች እንደሆኑ ይገመታል።የዘንድሮው ዓለም ዓቀፍ የሴቶች ቀን (March 8 በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ 113ኛ ጊዜ “invest in women accelerate progress እንዲሁም በሀገር አቀፍ ደረጃ ለ48ኛ ጊዜ “ሴቶችን እናብቃ ልማትና ሰላምን እናረጋግጥ በሚሉ መሪ ቃሎች እየተከበረ ይገኛል።See insights and adsBoost post

All reactions:1616