ጉባዔው በአንድ ሕገ መንግስታዊ ጉዳይ ላይ የውሳኔ ሀሳብ አሳለፈ
November 27, 2020
የሕገ መንግሥት አተረጓጎምና የውሳኔ አፈፃፀም ችግሮችን ለመፍታት ሁሉም አካል የራሱን ሀላፊነት መወጣት እንዳለበት ተጠቆመ
February 1, 2021

የጉባዔው ጽ/ቤት አመራርና ሠራተኞች የፀረ ሙስና ቀንን አከበሩ

????????????????????????????????????

የጉባዔው ጽ/ቤት አመራርና ሠራተኞች የፀረ ሙስና ቀንን አከበሩ

የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ ጽ/ቤት አመራርና ሠራተኞች የፀረ ሙስና ቀንን ዛሬ ህዳር 25/2013 የግንዛቤ ማስጨበጫ ውይይቶችን በማድረግ አከበሩ።

የጉባዔው ጽ/ቤት አመራርና ሠራተኞች በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ17 በሀገራችን ደግሞ ለ16 ጊዜ “የትውልድ የሥነ ምግባር ግንባታን በጠንካራ ዲሲፕሊን በመምራትና ሌብነትንና ብልሹ አሠራርን በመታገል የብልፅግና ጉዟችንን እናፋጥናለን!” በሚል መሪ ቃል በመከበር ላይ የሚገኘውን የፀረ- ሙስና ቀን በጽ/ቤቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ሲያከብሩ የመወያያ ፅሑፍ ቀርቦ ሠራተኞቹ ተወያይተውበታል።

በቀረበው የመወያያ ፅሑፍም የዓለም አቀፍ የፀረ ሙስና ኮንቬንሽን ላይ ያሉ ስምምነቶችና በአላማው ላይ የጠቀመጡ ዋና ዋና ይዘቶችን ጨምሮ በሀገራችን ሕግ ውስጥ የሙስና ሕጎች እና የሕግ ተጠያቂነቱ ምን እንደሚመስል በስፋት ተዳሷል። በዚህም ሀገራችን ኢትዮጵያ በኮንቬንሽኑ አላማ መሰረት የፀረ ሙስና ህጎችን በማወጣት የህግ ማእቀፍ ውስጥ ያስገባች ሲሆን አለም አቀፍ ትብብር ላይ እና የተመዘበሩ ሀብቶችን በማስመለስ ረገድ እንቅስቃሴዎች ቢኖሩም እጥረቶች ያሉ በመሆናቸው ሊሰራበት እንደሚገባ ተመልክቷል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ሀገራችን ኢትዮጵያ በአፍሪካና በዓለም ደረጃ ሙስናን በመዋጋት እና በሙስና መንሰራፋት ያለችበት ደረጃ የተዳሰሰ ሲሆን፣ ከዚሁ ጋር በተያያዘ ከሠራተኞች የተለያዩ ጥያቄዎች ተነስተው ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል።

በመጨረሻም በጉባዔው ጽ/ቤት የጉባዔውና የጽ/ቤት ኃላፊ ልዩ ረዳት የሆኑት አቶ ከበበ ታደሰ ሙስና ሀገር ላይ ከባድ አደጋ የሚያደርስ መሆኑን በመጥቀስ እንደተቋም ሲታይ ከገንዘብ ጋር በማያያዝ ብቻ ሳይሆን ሁሉም ለሚሰራው ስራ አንጻር ከጊዜና ከንብረት አጠቃቀምም ጋር አያይዞ በማየት ይህን የሙስና አደጋ ለመከላከል እንዲረባረብ አሳስበው ክብረ በዓሉ ተጠናቋል።

????????????????????????????????????

????????????????????????????????????

????????????????????????????????????