ጉባዔው በ 86 ሕገ መንግሥታዊ ጉዳዮች ላይ ውሳኔ አሳለፈ
July 11, 2022
የህፃናት ሕገ መንግሥታዊ መብት ከአሳዳጊዎቻቸው የሃይማኖት ነፃነት አንፃር
August 9, 2022

የጉባዔው ጽ/ቤት አመራርና ሠራተኞች አረንጓዴ አሻራቸውን አኖሩ

የጉባዔው ጽ/ቤት አመራርና ሠራተኞች አረንጓዴ አሻራቸውን ሲያኖሩ

የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ ጽ/ቤት አመራርና ሠራተኞች አራተኛውን ዙር ሀገራዊ የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር በማስመልከት በምሥራቅ ሸዋ ዞን አዳማ ወረዳ አዱላላ ሀጤ ሀሮሬቲ ቀበሌ በመገኘት ሐምሌ 29/2014 ዓ.ም አሻራቸውን አኖሩ።

አመራርና ሠራተኞቹ በቀበሌው በሚገኝ ኮረብታማ ቦታ ላይ ከ2 ሺህ በላይ ችግኞችን ከአካባቢው ነዋሪዎች ጋር በመቀናጀት ተክለዋል።

በተከላው ወቅት የጉባዔው ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ደሳለኝ ወዬሳን ጨምሮ የአዱላላ ሀጤ ሀሮሬቲ ቀበሌ አመራርና የልማት ሠራተኞች የተገኙ ሲሆን፣ የአረንጓዴ ልማት ሥራው ለአካባቢው ነዋሪ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው በማስታወስ ሁሉም ያለመታከት ሊንከባከበው እንደሚገባ ለነዋሪዎቹ አስገንዝበዋል። ጽ/ቤቱም ድጋፍና ክትትሉን ከዚህ በኋላም የሚቀጥል መሆኑን ገልፀዋል።

ጽ/ቤቱ ቦታውን በተከታታይ ዓመታት ለማልማት በ2012 ዓ.ም የተረከበው ሲሆን፣ ከተረከበበት ዓመት ጀምሮ ተራቁቶና ለመሸርሸር ተጋልጦ የነበረውን ኮረብታ በተከታታይ ዘመቻ ከማልማት ባሻገር ቦታው ከሰውና እንስሳት ንክኪ እንዲጠበቅ ጥበቃዎችን በመቅጠር ያልተቋረጠ እንክብካቤ በማድረግ ላይ ይገኛል።