‹አንቀጽ 84›

የሕገ መንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ ሥልጣንና ተግባር

 

  1. የሕገ መንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ ሕገ መንግስታዊ ጉዮችን የማጣራት ሥልጣን ይኖረዋል፡፡ በሚያደርገው ማጣራት መሰረት ህገ ምግስቱ መተርጎም አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው ለፌዴሬሽን ምክር ቤት በጉዳዩ ላይ የውሳኔ ሀሳብ ያቀርባል፡፡
  2. በፌዴራ መንግስትም ሆነ በክልል ሕግ አውጪ አካላት የሚወጡ ህጎች ከዚህ ህገ መንግስት ጋር ይቃረናሉ የሚል ጥያቄ ሲነሳና ጉዳም በሚመለከተው ፍርድ ቤት ወይም በባለ ጉዳዩ ሲቀርብለት መርምሮ ለመጨረሻ ውሳኔ ለፌዴሬሽኑ ምክር ቤት ያቀርባል፡፡
  3. በፍርድ ቤቶች የህገ ምግስት ትርጉም ጥያቄ ሲነሳ

ሀ/ ሕገ መንግስቱን መተርጎም አስፈላጊ ሆኖ ሳያገኘው ሲቀር ጉዳዩን ለሚመለከተው ፍርድ ቤት ይመልሳል በአጣሪ ጉባኤው ውሳኔ ቅር የተሰኘ ባለጉዳይ ቅሬታውን ለፌዴሬሽኑ ምክር ቤት በይግባኝ ማቅረብ ይችላል፡፡

ለ/ የትርጉም ጥያቄ መኖሩን ያመነበት እንደሆነ በጉዳ ላይ የሚሰጠውን  ሕገ መንግስታዊ ትርጉም ለፌዴራሽን ምክር ቤር ለመጨረሻ ውሳኔ ያቀርባል፡፡

  1. የሚመራበትን ሥነ ሥርዓት አርቅቆ ለፌዴሬሽኑ ምክር ቤት ያቀርባል ሲፈቀድም ተግባራዊ ያደርጋል፡፡