1. የውስጥ ኦዲት ዳይሬክቶሬት

የውስጥ ኦዲት ዳይሬክቶሬት ተግባርና ኃላፊነት

የውስጥ ኦዲት ዳይሬክቶሬት በተሠጠው የሥራ ተግባርና ኃላፊነት በፌደራል ገ/ኢ/ል/ሚ/ር መመሪያ 7/2003 ዓ/ም በፀደቀውና የፌደራል መንግሥት የውስጥ ኦዲተሮች አስተዳደር መመሪያ ቁጥር 47/2009 መሠረት በጽ/ቤት ውስጥ የውስጥ ቁጥጥር ሥርዓቱ በአግባቡ መዘርጋቱንና አፈፃፀሙም የፋይናንስን ደንብና መመሪያ በተከተለ መልኩ እየተፈፀመ መሆኑን፤ የገንዘብና ንብረት አያያዝ አጠባበቅና አመዘጋገብ እንዲሁም የአስተዳደራዊ ሥራዎች አፈፃፀም መንግሥት ባወጣቸው አዋጆች፤ ደንቦችና መመሪያዎች መሠረት በትክክል መፈፀማቸውን ክትትልና ቁጥጥር በማድረግ በኦዲት ግኝቶች ላይ የማሻሻያና የማስተካከያ እርምጃዎች እንዲወሰዱ በማድረግ አስተያየቶችንና የማስተካከያ ሀሳቦችን በሪፖርት ለበላይ ኃላፊ ያቀርባል፡፡

ዝርዝር ተግባራት

 • ቅድሚያ የሚሰጣቸዉ ተግባራትን ከመስሪያ ቤቱ ዓላማ ጋር የተጣጣሙ መሆናቸዉን ለማረጋገጥ/ሥጋት/ተጋላጭነት ያለባቸዉን ዕቅድ ከሰዉ ኃይል አመዳደብና ከወጪ በጀት ፍላጎት ጋር አጠቃሎ በማዘጋጀት ለመስሪያ ቤቱ የበላይ ኃላፊ አቅርቦ ማፀደቅና የኦዲት የሥራ ትዕዛዝ እና ሃሣብ በመስጠት እቅድና ፕሮግራም የማዘጋጀት፣
 • የፀደቀዉን እቅድ በዚህ መመሪያ አንቀፅ 89ንዑስ አንቀፅ2 በተመለከተዉ መሠረት አዘጋጅቶ ለሚኒስትሩ የማቅረብ፣/አስፈላጊዉን ዕዉቀት፣ ክህሎት እና ልምድ በሚያሟሉበት የሥራ መስክ እንዲሣተፉ ሊመቻችላቸዉ ይገባል፣
 • የኦዲት ዕቅድን ሁሉም ኦዲት ተደራግ የሥራ ክፍሎች እንዲያዉቁት የማድረግ፤
 • የኦዲት ሥራን በብቃት ለማከናወን የሚያስችላቸዉ ዕዉቀት፣ልምድ፣ክህሎትና ለሎች ተፈላጊ ችሎታዎች እንዲኖራቸዉ የማድረግና የሥልጠና ፍላጎቶችን በማቀድና በበላይ ኃላፊ በማፀደቅ አፈፃፀሙን የመከታተል፤
 • የመስሪያ ቤቱን ዓላማዎች በከፍተኛ ቁጠባና ዉጤታማ በሆነ መንገድ ከግብ ለማድረስ ማስቻሉን በቂ መረጃዎችን ሰብስቦ በመገምገምና በቁጥጥር ስርዓቱ ላይ ያለዉን ስጋት ወይም ተጋላጭነት በመለየት ለመስሪያ ቤቱ የበላይ ኃላፍ የማሳወቅ፣
 • የኦዲት መጀመሪያ ስብሰባ እና ኦዲቱን አከናዉኖ የኦዲት ማጠናቀቅያ ስብሰባ ከሚመለከታቸዉ ሠራተኞች የሥራ ኃላፊዎችና ከተቋሙ የበላይ ኃላፊ ማድረግ፣
 • የተደረሰበትን ዉጤት፣ድምዳሜና የማሻሻያ ሃሣብ በሪፖርት ላይ የተመሰረተ የተሟላ ሪፖርት አዘጋጅቶ ለመሥሪያ ቤቱ የበላይ ኃላፊ የማቅረብ፣
 • በዕቅድ ያልተያዘ ልዩ ኦዲት እንዲያደርግ በኃላፊ ሲታዘዝ ኦዲት የማከናወን፣

 

 ኃላፊነት

 • በበጀት ዓመቱ መጨረሻ በመስሪያ ቤቱ አማካኝነት የተደረገዉን ቆጠራ በፋይናንስ አስተዳደር አዋጅ፣ደንብና መመሪያዎች መሠረት መከናወኑን በማረጋገጥ የቆጠራ ሪፖርቱ ከቆጠራ ሰነድ ጋር ለኃላፊዉ እንዲቀርብ የማድረግ፣ይህንንም ለማረጋገጥ በቆጠራ ወቂት በታዛቢነት የመገኘት፣በፈሰስ ሂሣብ ሥራ ላይ የመሳተፍ፣
 • በኦዲት ሪፖርቶች መሠረት የእርምት እርምጃ ያልተወሰደባቸዉን ግኝቶች በመከታተል እርምጃ እንዲወሰዱባቸዉ ለተቋሙ ኃላፊ የማሣሰብ፣
 • የዉጪ ኦዲተሮች በሚያቀርቧቸዉ ግኝቶች ላይ የእርምት እርምጃዎች እንዲወሰዱ ክትትል የማድረግ፣
 • በዉስጥ ኦዲት የተከናወኑ ተግባራትን የሚገልጽ ወቅታዊና ዓመታዊ የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ለተቋሙ ኃላፊ የማቅረብ ኃላፊነት አለበት፡፡