የኮሙኒኬሽንና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዳይሬክቶሬት የሚሰጡ ዋና ዋና አገልግሎቶች (ተግባርና ሀላፊነት)

 

 • ተቋሙን የሚመለከቱ መረጃዎች ለአገልግሎት ዝግጁ በማድረግ ለልዩ ልዩ መረጃ ፈላጊዎች መረጃ ይሰጣል፣
 • ተቋሙን ለማስተዋወቅ የሚያስችል መልዕክት በማዘጋጀት በልዩ ልዩ መገናኛ ብዙሃን ያሰራጫል፣
 • እንደአስፈላጊነቱ ከፅ/ቤቱ ጋር በመነጋገር ጋዜጣዊ መግለጫ እንዲሰጥ ያደርጋል፣ ዜና መግለጫዎችን በማዘጋጀት ለሚዲያዎች ይልካል፣
 • የጉባኤውንና ተቋሙን ክንውኖች እንዲሁም መልእክቶች በልዩ ልዩ ህትመቶች (አመታዊ መፅሄት፣ ዜና መፅሄት፣ ብሮሸር፣ ጆርናል፣ ማስታወሻ ደብተር፣ እስክሪፕቶ፣ በራሪ ወረቀት፣ ባነር…) በማሳተም ያሰራጫል፣
 • ማህበራዊ ሚዲያዎችን በመጠቀም የጉባኤውንና የፅቤቱን የእለት ተእለት እንቅስቃሴ በዜናና መልእክት መልክ ለህብረተሰቡ ያሰራጫል፣ ስለተቋሙ የተዘገቡ ጉዳዮችን ሚዲያ ሞኒተር በማድረግ ይከታተላል፣ ምላሽ ለሚያስፈልገው እንዲሰጥ ያደርጋል፣
 • የጉባኤውና የንኡስ ጉባኤው ቃለጉባኤዎች በሀርድና ሶፍት ኮፒ እንዲያዙ ያደርጋል፡፡ በሀርድ ኮፒው ላይ የጉባኤው አባላት ፈርመውባቸው ተጠርዘው በሰነድ መልክ እንዲቀመጡ ደርጋል፣
 • በተቋሙ የሚካሄዱና ከተለያዩ አካላት ጋር የሚካሄዱ መድረኮችን ያመቻቻል፣ ያስተባብራል ይመራል፣
 • የተቋሙ የስራ ክፍሎች የቤተመፃህፍት አገልግሎት እንዲያገኙ ያደርጋል፣ ቤተመፃህፍቱንም በማዘመን ቀልጣፋ አገልግሎት ይሰጣል፡፡
 • የተቋሙ የስራ ክፍሎች የተለያዩ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን እንዲጠቀሙ የሚያስችል ሲስተም በመፍጠር ስራቸውን እንዲያቀላጥፉ ያግዛል፣
 • ለስራ ክፍሎች እንደፍላጎታቸው የተለያዩ የኮምፒውተርና ተዛማጅ እቃዎች ግዥና ጥገና የቴክኒክ ድጋፍ፣ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ስልጠና ይሰጣል፣
 • አዳዲስ የኢንፎርሜሽንና ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂዎችን ወደ ተቋሙ በማምጣት ተቋሙ እንዲጠቀምበት ያደርጋል፣
 • ከሀገር ውስጥ እና ከውጭ አገር ተቋማት ጋር አጋርነትን ያጠናክራል፡፡

 

 

 

 ይርጋዓለም ጥላሁን አስረስ
 የኢንፎርሜሽንና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ተ/ዳይሬክተር
የትምህርት ደረጃ፡- ዲግሪ በህግ፣  ቋንቋና ስነፅሁፍ
ስልክ፤- 0911742232
ኢሜይል፡- yirgalemtilahun1@yahoo.com