አጣሪ ጉባኤው መደበኛ ጉባኤውን አካሄደ
September 10, 2018
የሕገ መንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ ጽ/ቤት ሰራተኞች የሰንደቅ አላማ ቀንን በደማቅ ሁኔታ አከበሩ
October 16, 2018

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የሕገ መንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ አርባ አቤቱታዎችን መርምሮ የውሳኔ ሀሳብ አቀረበ

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የሕገ መንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ መስከረም 3 እና 4 2011 ዓ/ም በአዳማ ከተማ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ የሕገ መንግስት ትርጉም የሚያስፈልገው አንድ አቤቱታ ትርጉም እንዲሰጥበት ለፌደሬሽን ምክር ቤት አቀረበ፡፡

የተለያዩ አካላት የሕገ መንግስት መብታችን ተጥሷልና ጉዳዩ ይጣራልን በማለት ለጉባኤው ያቀረቡ ሲሆን ጉባኤውም የቀረቡለትን አርባ አቤቱታዎች መርምሮ ውይይት ካደረገ በኋላ ከአቤቱታዎቹ መካከል አንዱ የህገ መንግስቱ አንቀጽ 40 የዜጎች ንብረት የማፍራት መብትን የጣሰ ሆኖ ስላገኘው የሕገ መንግስት ትርጉም ያስፈልገዋል ሲል ሕገ መንግስቱን የመተርጎም ስልጣን የተሰጠው የፌዴሬሽን ምክር ቤት ትርጉም እንዲሰጥበት የውሳኔ ሃሳብ አቅርቧል

በተጨማሪም ጉባኤው ቀሪዎቹ ሰላሳ ዘጠኝ አቤቱታዎች በዝርዝር ከተወያየ በኋላ በየደረጃው የተሰጡ የፍርድ ቤት ውሳኔዎች የህገመንግስት ጥሰት ያልታየባቸው በመሆኑ የሕገ መንግስት ትርጉም አያስፈልጋቸውም በማለት ውሳኔ ሰጥቷል፡፡