የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ደንብ ቁጥር 155/2000 አንቀፅ 37 ከሕገ መንግሥቱ አንቀፅ 37/1/ ጋር የሚጋጭ መሆኑ ተገለጸ
February 14, 2019
የጨረታ ማስታወቂያ
April 19, 2019

የሕገ መንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ ልዑካን ቡድን በኮትዲቯር ኮንፍረንስ ላይ ተሳተፈ

በምክትል ሰብሳቢው ክቡር አቶ ሠለሞን አረዳ የተመራው የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ ልዑካን ቡድን የጀርመን ኢኮኖሚ ትብብርና ልማት ሚኒስቴር እ.ኤ.አ ከጥር 27 እስከ ጥር 28 ቀን 2011 ዓ.ም ድረስ በኮትዲቯር ርዕሰ ከተማ አቢጃን በተዘጋጀው ኮንፍረንስ ላይ በመሳተፍ የልምድ ልውውጥ አደረገ።

ኮንፍረንሱ “ተደራሽነት ለፍትህና ዳኝነት መጠናከር” (Conference on Access to Justice and Judicial Integrity) በሚል ጭብጥ የተካሄደ ሲሆን፣ የአፍሪካ ሀገራት ፍርድ ቤቶችና የሕገ መንግሥት ተርጓሚ ተቋማት አመራሮች እንዲሁም ከአውሮፓ የተጋበዙ ሀገራት የተጋበዙ ዳኞችና አመራሮች ተሳትፈውበታል። በኮንፍረንሱ ውይይት ላይ የተለያዩ ጽሁፎች የቀረቡ ሲሆን፣ በመጀመሪያው ቀን “የዳኝነት መጠናከርን  ማስተዋወቅ” በሚል ርዕስ በጀርመን የፋይናንስ ፍርድ ቤት ፕሬዚደንት ፐሮፌሰር ማሊንግሆፍ ፅሑፍ ቀርቦ ውይይት ተካሂዶበታል።

በሁለተኛው የውይይት ቀን “ፍትህን ለሁሉም አካላት ተደራሽ ማድረግ” እና “ሁለንተናዊ ተደራሽነት ለትክክለኛ ፍትህ በአፍሪካ” የሚሉ ፅሑፎች ቀርበው፣ በተለይ የዲጂታል ቴክኖሎጂዎችን ተጠቅሞ ፍትህን ለሁሉም አካላት ተደራሽ በማድረግ ላይ ሰፊ ውይይት የተደረገ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ ተሞክሮም ቀርቧል። የኮንፈረንሱ ተሳታፊዎችም የየሀገራቸውን ተሞክሮ በማቅረብ ውይይት ተደርጎበታል። ከማኅበራዊ ድረ ገጾች እንደ ፌስቡክ ያሉትም ቢሆኑ የራሳቸው ደካማ ጎን ቢኖራቸውም በአግባቡ በመጠቀም ለበርካታ አካላት ተደራሽ ለማድረግ እንደሚያስችሉ በብዙዎቹ ታምኖበታል።

በኮንፍረንሱ ላይ ሀገራችንን ወክለው ከተሳተፉት መካከል የጉባዔውና የጽ/ቤት ኃላፊ ልዩ ረዳት አቶ ከበበ ታደሰ እንደገለጹልን በአቢጃን የተካሄደው ኮንፍረንስ በአፍሪካ ብሎም በኢትዮጵያ የፍትህ ስርዓትን ከማጠናከር ባሻገር ድርሻው የጎላ በመሆኑ ከፍተኛ ልምድ የተቀሰመበት መሆኑን ጠቁመው፣ በእንደዚህ ዓይነት የልምድ ልውውጦች ላይ የሀገራችን  ተሳትፎ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልና የተገኘውንም ተሞክሮ ወደ ተቋሞቻችን አሠራር በማምጣት አዎንታዊ ለውጥ መፍጠር እንደሚቻል አስታውቀዋል።