ጉባዔው መስከረም 21/2012 ዓ.ም ባደረገው ጉባዔ ሁለት ጉዳዮች የሕገ መንግሥት ትርጉም እንዲሰጥባቸው ለፌ/ም/ቤት የውሳኔ ሃሳብ አቀረበ
October 3, 2019
ለቃሊቲ ኮንስትራክሽን ዕቃዎች ማምረቻ ፋብሪካ ሴት ሰራተኞች በሴቶች መብቶች ዙሪያ ስልጠና ተሰጠ
November 20, 2019

የሕገ መንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ ጽ/ቤት ለፌደሬሽን ምክር ቤት አባላት ስልጠና ሰጠ

????????????????????????????????????

የሕገ መንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ ጽ/ቤት ለፌደሬሽን ምክር ቤት አባላት ስልጠና ሰጠ

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የሕገ መንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ ጽ/ቤት “በሕገ መንግስት አተረጓጎም መርሆችና ስርአት” እና “የገጠር መሬት ማስተላለፍ ከኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሕገ መንግስት አንፃር” በሚል ርዕስ መስከረም 28 ቀን 2012 ዓ/ም የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የፌደሬሽን ምክር ቤት አዘጋጅነት በፍሬንድሺፕ ሆቴል ላይ የአንድ ቀን ስልጠና ሰጠ፡፡

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የሕገ መንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ደሳለኝ ወዬሳ “በሕገ መንግስት አተረጓጎም መርሆችና ስርአት” ላይ ስልጠናውን የሰጡ ሲሆን፣ የጽ/ቤቱ የጥናትና ምርምር ባለሙያ የሆኑት አቶ ያደታ ግዛውና  አቶ መሀመድ መብራት “የገጠር መሬት ማስተላለፍ ከኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሕገ መንግስት አንፃር” በሚለው ርእስ ላይ ለምክር ቤቱ አባላት  ስልጠና ሰጥተዋል፡፡

በስልጠናው ከተሳታፊዎች አስተያቶችና ጥያቄዎች ቀርቦ ጽሁፍ አቅራቢዎችም ምላሽ የሰጡበት ሲሆን እንዲህ አይነት ስልጠናዎች ሰፊ ጊዜ የሚፈልጉና ጊዜ የሚወስዱ በመሆናቸው ስልጠናው ሰፊ ፕሮግራም ተይዞ ቢሰጥ የሚል አጠቃላይ አስተያየት ከተሳታፊዎች ቀርቧል፡፡