በኢትዮጵያ የሕገ መንግሥት ትርጉም ስርዓት የመገናኛ ብዙሃን ሚና በሚል ርዕስ ከዘርፉ ባለሙያዎች ጋር ውይይት ተካሄደ
July 13, 2021
የጽ/ቤቱ ሠራተኞች ለሕልውና ዘመቻው የሚጠበቅባቸውን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁነታቸውን ገለጹ
August 17, 2021

የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ ጽ/ቤት አመራርና ሠራተኞች የ3ተኛውን ዙር የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር አከናወኑ

የጽ/ቤቱ አመራርና ሠራተኞች ከአዳማ ወረዳ አዱላላ ሀጤ ሀሮሬቱ ቀበሌ ከዚህ ቀደም ለማልማት የተረከቡት ገላጣ ጋራ ላይ ለሁለተኛ ጊዜ አረንጓዴ የማልበስ ሥራን ሐምሌ 16/2013 ዓ.ም አከናውነዋል፡፡

በችግኝ ተከላው ላይ ከጽ/ቤቱ አመራርና ሠራተኞች በተጨማሪ የወረዳውና የቀበሌው የሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም የአካባቢው ነዋሪዎች ተገኝተዋል፡፡

በዕለቱ ከአካባቢው አየርና ከአፈሩ ሁኔታ ጋር ተስማሚ የሆኑ ከ1 ሺህ በላይ አዳዲስ ችግኞች የተተከሉ ሲሆን፣ አምና በተመሳሳይ ወቅት የተተከሉ ችግኞችንም የመኮትኮትና የመንከባከብ ሥራ ተሠርቷል፡፡

ከችግኝ ተከላው በኋላ የጉባዔው ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ደሳለኝ ወዬሳ ለኑሮ ምቹ ከባቢን ለመፍጠር የጉባዔው ጽ/ቤት ድጋፉን ሳያቋርጥ እንደሚሠራ ጠቁመው፣ የአካባቢው ማኅበረሰብም ልማቱ የራሱ መሆኑን አውቆ እንክብካቤና ጥበቃውን ሊያጠናክር እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

የቀበሌው ሊቀመንበርና  የወረዳው ኃላፊም መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን፣ ለሚደረገው የአረንጔዴ ልማት ሥራም ምስጋና አቅርበዋል፡፡