የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ
September 8, 2022
ጉባዔው 137 ሕገ መንግሥታዊ አቤቱታዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ።
September 22, 2022

የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ ጽ/ቤት አመራሮችና ሠራተኞች ለጀግናው መከላከያ ሠራዊታችን ደም ለገሱ።

መስከረም 9 ቀን 2015 ዓ.ም (አዲስ አበባ)

“ደማችን ለመከላከያ ሠራዊታችን” በሚል መሪ ቃል የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት፣ የፌዴሬሽን ም/ቤትና የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ ጽ/ቤት የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች የኢትዮጵያን ክብርና ሉዓላዊነት ለማስከበር በግንባር ትግል እያደረገ ለሚገኘው ለጀግናው መከላከያ ሠራዊታችን የደም ልገሳ መርሃ ግብር አከናውነዋል።

በደም ልገሳ መርሃ ግብሩ ላይ የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ ጽ/ቤት የሥራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ተገኝተው ደማቸውን ለጀግናው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ለግሰዋል። በሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ ጽ/ቤት የሰው ሃብት ልማት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር  አቶ ዮሐንስ ደሳለኝ እንደተናገሩት ጀግናው መከላከያ ሠራዊታችን በግንባር እያደረገው ለሚገኘው ተጋድሎ እኔም ለሀገሬ ውዱን ስጦታ ደሜን ለግሻለሁ ብለዋል።  አቶ ዮሐንስ አክለውም ኢትዮጵያዊነት ለወዳጅም ሆነ ለጠላት መስጠት፣ መለገስ ነው ያሉ ሲሆን እንደ ጽ/ቤት ለ2ኛ ጊዜ ደም ልገሳ መደረጉን አውስተዋል። ወደፊትም ለጀግናው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የሚደረገው ድጋፍ በንቃትና በሞራል ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የገለፁት አቶ ዮሐንስ ለጀግናው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ደም በመለገሳቸው ኩራትና ደስታ እንደሚሰማቸው ገልፀዋል። 

ሌላኛዋ በደም ልገሳ ፕሮግራሙ ላይ የተሳተፈችው ወጣት ገነት ማርቆስ ለጀግናው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ደም በመለገሷ ታላቅ ደስታ እንደተሰማት ገልፃለች። ከዚህ በፊት ደም ለመለገስ ብፈልግም ፍርሃት ስለነበረብኝ አልሰጠሁም፤ ዛሬ ለመጀመሪያ ጊዜ ተሳክቶልኛል ያለችው ወጣት ገነት ሁሉም ሰው ሳይፈራ ደም እንዲለግስ መልዕክቷን አስተላልፋለች።