የኢ.ፌዴ.ሪ የህገ መንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ አባላት ለጉባኤው ሰብሳቢና ም/ሰብሳቢ  የአቀባብል ስነ ሥርዓት አካሄዱ
November 15, 2018
በሀገር ዓቀፍ ደረጃ የሕገ መንግሥት አተረጓጎም ሥርዓትን ለማጠናከር የሚያስችል የምክክር መድረክ ተካሄደ
December 31, 2018

የሕገ መንገስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ ጽ/ቤት ሰራተኞች ፀረ-ፆታዊ ጥቃት ቀንን በማስመልከት ውይይት አካሄዱ

አሳዳጊ የሌላቸውን ህጻናት ለማሳደግም እናት አምባሳደር መርጠዋል!

የህገ መንገስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ ጽ/ቤት ሰራተኞች ከህዳር 15 እስከ 30 2011 ዓ.ም በአለም ለ 27ኛ በሀገራችን ለ13ኛ ጊዜ የሚከበረውን የፀረ-ፆታዊ ጥቃት ቀን በማስመልከት ህዳር 15 ቀን 2011 ዓ.ም በአለም ገና ከተማ ውይይት አካሂደዋል፡፡

በዕለቱ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአጣሪ ጉባኤ ጽ/ቤት ተወካይ አቶ ጌታቸው ጉዲና የሴቶችን ጥቃት መከላከል የተጀመረውን ለውጥ ለማስቀጠል አንዱና ዋነኛው ተግባር እንደሆነ ገልፀዋል፡፡ የመክፈቻ ንግግሩን ተከትሎ እለቱን የተመለከቱ የተለያዩ የመወያያ ፅሁፎች ቀርበዋል፡፡ በሴቶች፣ ወጣቶችና እና ህፃናት ላይ የሚፈፀሙ ፆታዊ ጥቃቶች በወ/ሮ አስቴር ተሰማ፤ የሴቶችና ህፃናት መብት በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሕገ መንግስት አቶ ጌታቸው ጉዲና እንዲሁም የህፃናት መብት ከኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሕገ መንግስትና ከተለያዩ አለም አቀፍ ህጎችና ስምምነቶች አንፃር በወ/ሪት ራሄል ብርሃኑ ቀርቧል፡፡ በዕለቱ አስተማሪ የሆኑና የሴቶችን ጥቃት የሚያሳዩ ቪዲዮዎችም ለዕይታ ቀርበዋል፡፡

በውይይቱ ከተሳታፊዎች የተለያዩ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ተነስተዋል የሴቶችን ጥቃት ለመከላከል የሚያስችል ስራ በበቂ ሁኔታ በሚዲያ እየተሰራ እንዳልሆና የሴቶችና ህጣነት ጥቃት ከጊዜ ወደ ጊዜ መልኩን እየቀያየረ እየጨመረ እንደሆነ፣ የሴቶችና ህፃናትን ጥቃት የሚያበረታቱ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች ላይ በሰፊው መሰራት እንዳለበት፣ በሴቶች ላይ ጥቃት የሚፈፅሙ ግለሰቦችና ቡድኖች ላይ አስተማሪና የማያዳግሙ ዕርምጃዎች አለመወሰዳቸው፣ ከወሬ የዘለለ በተግባር የሚታይ የሴቶችን ጥቃት ለመከላከል የሚሰሩ ተቋማት አለመስፋፋታቸው፣ የሴቶችና ህፃናትን ጥቃት ለመከላከል የህግ ክፍተቶችን የሚሞላ አሰራር መዘርጋት እንሚኖርበት ተጠቁሟል፡፡

ለተነሱት አስተያየቶችና ጥያቄዎች የመወያያ ፅሁፍ አቅራቢዎቹ ምላሾችን ሰጥተዋል፡፡

በውይይቱ ከተያዙት አጀንዳዎች በተጨማሪ የጽ/ቤቱ ሰራተኞች ሁለት አሳዳጊ የሌላቸው ህፃናትን ለማሳደግ የተስማሙ ሲሆን ሕፃናቱ የሚገኙበትን ሁኔታ የምትከታተል እናት አምባሰደርም መርጠዋል፡፡

በመጨረሻም የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ ደሳለኝ ወዬሳ ሁላችንም ካልተባበርን የሴቶችን ጥቃት መከላከል እንደማይቻል፣ መንግስት የሴቶችን ጥቃት ለመከላከል ህግ ማውጣት ብቻ በቂ እንዳልሆነና ህብረተሰቡን ባሳተፈ መልኩ መስራት እንዳለበት በማጠቃለያ ንግግራቸው ገልፀዋል፡፡