የዓለም አቀፉ ሕገ መንግስታዊ ፍርድ ቤቶች ዋና ጸሀፊ ኢትዮጵያን ጎበኙ
June 20, 2019
ኢትዮጵያ የአፍሪካ ሕገ መንግስታዊ ፍ/ቤቶችና መሰል ተቋማት ስራ አስፈፃሚ ቢሮ አባል ሆና ተመረጠች
July 2, 2019

የሀዘን መግለጫ

????????????????????????????????????

የሀዘን መግለጫ

በአማራ ክልል በተፈፀመው የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ የአማራ ክልል መስተዳድር ክቡር ዶክተር አምባቸው መኮንንና የህዝብ አደረጃጀት አማካሪያቸው ክቡር አቶ እዘዝ ዋሴ ህይወታቸውን በማጣታቸውና እንዲሁም የኢፌዴሪ መከላከያ ጠቅላይ ኢታማጆር ሹም ጄነራል ሰአረ መኮንንና ሜጀር ጄነራል ገዛኢ አበራ ላይ በደረሰው ጥቃት ህይወታቸው በማለፉ የሕገ መንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ  እና የጉባኤው ፅ/ቤት ሰራተኞች የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ይገልፃሉ፡፡

????????????????????????????????????

ክቡር ዶክተር አምባቸው መኮንን የሕገ መንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ አባል ሆነው ከተመረጡ ጊዜ ጀምሮ ከጉባኤው አባላት ጋር በመሆን የሕገ መንግስት የበላይነትን ለማስከበር ከፍተኛ አስተዋፅኦ ሲያደርጉ የነበሩ መሆናቸውን እየገለፅን በደረሰው ሀዘን ለሟቾች ቤተሰቦች እና ወዳጆቻቸው እንዲሁም ለኢትዮጵያ ህዝብ መፅናናትን እንመኛለን፡፡