በጋብቻ ውስጥ ባልና ሚስት የሚያደርጉት የንብረት ስምምነትና ሕገ መንግሥታዊ ጥበቃው
January 29, 2024
ጉባዔው ሦስተኛውን የመሰማት መድረክ አካሄደ።
March 27, 2024
Show all

ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት የአፍሪካ ሕገ መንግሥታዊ ፍ/ቤት ዋና ፀሐፊን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ።

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ ሰብሳቢ እና የፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት የአፍሪካ ሕገ መንግሥታዊ ፍ/ቤት ዋና ፀሐፊ የሆኑትን ሙሳ ላራባን የካቲት 8 ቀን 2016 ዓ.ምበጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።ከዚህ ቀደም እ.ኤ.አ በ2014 ወደ አዲስ አበባ መጥተው እንደነበር ያወሱት ዋና ፀሐፊው የአፍሪካ ሕብረት ስብሰባን ለመካፈል ግን ለመጀመሪያ ጊዜ እንደመጡ እና በከተማዋም በተለይ በግንባታው ዘርፍ ከፍተኛ ለውጥ መኖሩን አስረድተዋል። ሚስተር ሙሳ ላራባ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሙዝዬምን መጎብኘት እንደሚፈልጉ ለክቡር አቶ ቴዎድሮስ የገለፁላቸው ሲሆን በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይም ውይይት አድርገዋል።ክቡር አቶ ቴዎድሮስም በመዲናችን አዲስ አበባ ከተማ የአፍሪካ ሕገ መንግሥታዊ ፍ/ቤት ቅርንጫፍ ጽ/ቤት እንዲከፈት ለሚስተር ላራባ ጥያቄ ያቀረቡላቸው ሲሆን እሳቸውም ቢያንስ በሕገ መንግሥታዊ ፍ/ቤቱ እና በአፍሪካ ሕብረት መካከል ግንኙነት የሚፈጥር አንድ አመቻቺ (focal personnel) እንዲኖር እንደሚሠሩ ተናግረዋል።በቀጣይ የሚኖረውን የአፍሪካ ሕገ መንግሥታዊ ፍ/ቤት ውይይት ዚምባብዌ እንደምታስተናግድ የገለፁት ዋና ፀሃፊው፤ ለክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት እና ለሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ ጽ/ቤት ኃላፊው ለአቶ ደሳለኝ ወዬሳ የአፍሪካ ሕገ መንግሥታዊ ፍ/ቤትን አርማ የያዘ ስጦታን አበርክተዋል።የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ እ.ኤ.አ ማርች 15, 2017 የተቀላቀለው የአፍሪካ ሕገ መንግሥታዊ ፍ/ቤት 47 የአፍሪካ ሀገራትን ሕገ መንግሥታዊ ተቋማት በአባልነት ያቀፈ ሲሆን አፍሪካዊ ያልሆኑ የ4 ሀገራትን ሕገ መንግሥታዊ ተቋማት በታዛቢነት አካቷል። እነዚህ በታዛቢነት የተካተቱ 4 ሀገራትም ብራዚል፣ ቱርክ፣ ሩስያ እና ኢራቅ መሆናቸው ይታወሳል።See insights and adsBoost post

All reactions:6363