ጉባዔው መስከረም 21/2012 ዓ.ም ባደረገው ጉባዔ ሁለት ጉዳዮች የሕገ መንግሥት ትርጉም እንዲሰጥባቸው ለፌ/ም/ቤት የውሳኔ ሃሳብ አቀረበ
October 3, 2019

ከኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሕገ መንግሥት መሰረታዊ መርሆች አንዱ “የመንግሥት አሠራርና ተጠያቂነት” የሚለው በአንቀፅ 12 ተደንግጎ የሚገኘው ነው። በዚሁ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ 1 ስር “የመንግሥት አሠራር ለሕዝብ ግልፅ በሆነ መንገድ መከናወን አለበት” በማለት ያብራራል።

ከኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሕገ መንግሥት መሰረታዊ መርሆች አንዱ “የመንግሥት አሠራርና ተጠያቂነት” የሚለው በአንቀፅ 12 ተደንግጎ የሚገኘው ነው። በዚሁ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ 1 ስር “የመንግሥት አሠራር ለሕዝብ ግልፅ በሆነ መንገድ መከናወን አለበት” በማለት ያብራራል።

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ምክንያት 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ በወቅቱ መካሄድ ካለመቻሉ ጋር ተያይዞ የሕገ መንግሥት ትርጉም እንዲሰጥበት ለሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ ግንቦት 28/2012 ጥያቄ አቅርቧል።

ጉባዔውም ጥያቄውን ከተቀበለ በኋላ በጉዳዩ ላይ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የሚመለከታቸውን አካላትና ባለሙያዎችን በመጋበዝ አስተያየት ሲሰማና ግብዓት ሲሰበስብ፣ ከዚህ በፊት በታሪካችን ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ሂደቱን ግልፅ በሆነ መንገድ በመገናኛ ብዙኃን እንዲተላለፍ በማድረግ መላው ሕዝብ ሲከታተለው እንደነበር ይታወሳል።

በሂደቱም በሕገ መንግሥት ትርጉም ላይ ጉልህ ፋይዳ ሊያመጡ የሚችሉ ግብዓቶች ሊገኙ ችለዋል። ሂደቱንም ተከትሎ ጉባዔው በበቂ ትንተናና አሳማኝ ምክንያቶች ላይ ተመስርቶ ባደረገው ጥልቅ ማጣራት ጉዳዩ የሕገ መንግሥት ትርጉም የሚያስፈልገው ሆኖ ስላገኘው ለመጨረሻ ውሳኔ ወደ ፌዴሬሽን ምክር ቤት ግንቦት 21/2012 የውሳኔ ሀሳቡን ሊልክ ችሏል።

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፌዴሬሽን ምክር ቤትም ጉዳዩን ከመረመረና በምክር ቤቱ አባላት ሰፊ ውይይት ከተደረገበት በኋላ፣ ሰኔ 03/2012 በምክር ቤቱ 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ስብሰባው የጉባዔውን የውሳኔ ሀሳብ በማፅደቅ በጉዳዩ ላይ የሕገ መንግሥት ትርጉም ሰጥቶበታል።

በዚሁ መሰረት ከላይ በመግቢያው ላይ እንደተጠቀሰው የመንግሥትን አሠራር ግልፅ ለማድረግና መላው ሕዝብ የሂደቱን ነፃነት እንዲያውቅ ሙሉ አካሄዱን የሚያሳየውን ማለትም፡- የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ግንቦት 21/2012 የላከውን የውሳኔ ሀሳብ 31 ገፅ ሙሉውን ሰነድ ‘ስካን’ በማድረግ ከዚህ በታች ለአንባቢያን ግልፅ እንዲሆን ተጭኗል።

በዚህም የተከበራችሁ የድረ ገፃችንና የፌስ ቡክ ገፃችን ተከታታዮች ጠቃሚ መረጃ እንደምታገኙ ተስፋ እናደርጋለን።

PDF ->> https://www.cci.gov.et/wp-content/uploads/2020/06/CCI-Recomendation-Jun-06-2020.pdf