እንኳን ደስ አለን! ….ዛሬ ታህሳስ 10 ቀን 2012 ዓ.ም ንጋት ላይ ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ /ETRSS-1/ የተሰኘችውን የመሬት ምልከታ ሳተላይት ከቻይና ቤጂንግ ማስወንጨፊያ ጣቢያ ወደ ህዋ በተሳካ ሁኔታ በማምጠቋ የሕገ መንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ አመራሮችና ሰራተኞች የተሰማንን ደስታ እንገልፃለን፡፡
December 20, 2019
የክልል የፍትህ አካላትን ማጠናከር ለዜጎች የተፋጠነ ፍትህን ለመስጠት ወሳኝ መሆኑ ተገለፀ
January 22, 2020

ከሕገ መንግስት አተረጓጎም ጋር ተያይዞ በተጠኑ ጉዳዮች ላይ ከአማራብ/ክ/መ ክልል ዳኞች ጋር ውይይት ተደረገ

ከሕገ መንግስት አተረጓጎም ጋር ተያይዞ በተጠኑ ጉዳዮች ላይ ከአማራብ/ክ/መ ክልል ዳኞች ጋር ውይይት ተደረገ

የሕገ መንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ ጽ/ቤት “የመሬት ይዞታ ስለሚተላለፍበት አግባብ፣ ከአንድ በላይ ጋብቻ በሚኖርበት ጊዜ የንብረት ክፍፍልና ሳይፋቱ ፍቺ ከኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሕገ መንግስት አንፃር እንዲሁም ከፍርድ ቤቶች የሚላኩ የሕገ መንግስት ትርጉም ጥያቄዎች ምንነትና አተገባበር በሚሉ አርዕስቶች ዙሪያ ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት አመራሮችና ዳኞች እንዲሁም ከክልሉ ጠቅላይ አቃቤ ሕግ አመራሮች ጋር ከታህሳስ 19 – 20/2012 ዓ.ም በጎንደር ከተማ ምክክር ተካሄደ፡፡

በዕለቱ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የሕገ መንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ደሳለኝ ወዬሳ አጣሪ ጉባኤው ከቀን ወደቀን እየጨመረ የመጣውን አቤቱታ በተገቢው መንገድ በማጣራት አጣሪ ጉባኤው ለባለጉዳዮች ፈጣን ምላሽ ለመስጠት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ገልፀው የክልሉ ዳኞችም የዜጎችን ሕገ መንግስታዊ መብት በማስከበር ረገድ እስከዛሬ ሲያደርጉት የነበረውን አስተዋፅኦ በማጠናከር የዜጎችን መብት በጋራ ማስከበር እንደሚገባ ገልፀው እንግዶችን አንኳን ደህና መጣችሁ በማለት መልዕክታቸውን አስተላለፈዋል፡፡

በዕለቱ መድረኩን የከፈቱት የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ አብዬ ካሳሁን በክልልም ሆነ በፌደራል የሚወጡ ህጎች ላይ የሕገ መንግስት ትርጉም ጥያቄ ሲነሳ መርምሮ ውሳኔ የሚሰጠው አካል ማን ይሁን በሚለው ጉዳይ ላይ አገራት የተለያዬ አቋም እንዳላቸው ገልፀው አንዳንድ አገራት ለመደበኛ ፍርድ ቤት ስልጣኑን የሚሰጡ ሲሆን ሌሎች ደግሞ ሕገ መንግስቱን የሚተረጉም ስልጣንን ሌላ አካል ይሰጣሉ፡፡ የኢትዮጵያ ተሞክሮ ደግሞ ሕገ መንግስቱን የመተርጎም ስልጣን የተሰጠው ለፌደሬሽን ምክር ቤት ሲሆን ምክር ቤቱም ሕገ መንግስቱን የሚተረጉመው ከሕገ መንግስት አጣሪ ጉባኤ የውሳኔ ሃሳብ ሲቀርብለት አንደሆነ ገልፀዋል፡፡ አስከትለውም አሁን ያለንበት ዘመን ዜጎች መብታቸውን አጥብቀው የሚጠይቁበት ጊዜ በመሆኑ ሁላችንም ሕጉንና ሕገ መንግስቱን አክብሮ የማስከበር ኃላፊነታችንን ከሁልጊዜው በበለጠ መወጣት እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡

በመቀጠል የገጠር መሬት ይዞታ ስለሚተላለፍበት አግባብ ከኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሕገ መንግስት አንፃር እንዲሁም ከፍርድ ቤቶች የሚላኩ የሕገ መንግስት ትርጉም ጥያቄዎች ምንነትና አተገባበር በሚሉ አርዕስቶች በአቶ ያደታ ግዛው የሕገ መንግስት አስምህሮ ቡድን መሪ፣ ሳይፋቱ ፍቺ ከኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሕገ መንግስት አንፃር በጥናትና ምርምር ዳይሬክተሩ አቶ ጌታቸው ጉዲና እና ከአንድ በላይ ጋብቻ በሚኖርበት ጊዜ የንብረት ክፍፍል ከኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሕገ መንግስት አንፃር በወ/ሪት ራሄል ብርሃኑ የጉዳዮች ፍሰት አስተዳደር ዳይሬክተር የጥናት ፅሁፎች በሁለቱም ቀናቶች የቀረቡ ሲሆን ከመድረኩ ተሳታፊዎች በርካታ ጥያቄዎችና አስተያቶች ተነስተው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡

መድረኩን የማጠቃለያ ንግግር በማድረግ የዘጉት ክቡር አቶ ክፍለፅዮን ማሞ የሕገ መንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ የዜጎችን ሕገ መንግስታዊ መብቶች ለማስከበር ከፖለቲካ ተፅዕኖ ነፃ ሆኖ   ተግቶ እየሰራ ያለ ተቋም እንደሆነ ጠቁመው ጉባኤው በርካታ ጥናቶች እንዲጠኑ በማድረግ ከክልሎች ጋር ውይይት ማድረጉ ችግሮችን ለመፍታት እንደሚያስችል ገልፀው  በዚህም ውይይት በርካታ ትምህርቶችና ለጥናቶቹም ጥሩ ግብአቶች አንደተገኙ ገልፀዋል፡፡