አጣሪ ጉባዔው በየጊዜው የተሻለ ሥራ እየሠራ መሆኑን ዕውቅና መስጠት እፈልጋለሁ ሲሉ የፌዴሬሽን ም/ቤት አፈ ጉባዔ የተከበሩ አቶ አገኘሁ ተሻገር ተናገሩ።
March 27, 2024
አጣሪ ጉባዔው በ32 የሕገ መንግሥት የትርጉም አቤቱታዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ እና አቅጣጫ አስቀመጠ።
May 17, 2024
Show all

አጣሪ ጉባዔው በ50 የሕገ መንግሥት ትርጉም አቤቱታዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ ሰጠ።

የኢፌዴሪ የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ ሐሙስ መጋቢት 12 ቀን 2016 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ፤ በንዑስ አጣሪ ጉባዔ እና በአጣሪ ጉባዔ ጽ/ቤቱ የሕግ ተመራማሪዎች ሰፊ ጥናት እና ማጣራት ተደርጎባቸው ከቀረቡለት የሕገ መንግሥት ትርጉም አቤቱታዎች መካከል በቁጥር 50 በሚሆኑ አቤቱታዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ፣ የውሳኔ ሐሳብና አቅጣጫ አስቀምጧል።ጉባዔው በዕለቱ ከተወያዬባቸው ጉዳዮች መካከል በቁጥር 46 የሚሆኑ አቤቱታዎች ሕገ መንግሥታዊ ጥሰት አልተፈፀመባቸውም በሚል እንዲዘጉ ውሳኔ አሳልፏል።በሌላ በኩል “ፍትሕ የማግኘት እንዲሁም የእኩልነት እና የንብረት ሕገ መንግሥታዊ መብቴ ተጥሷል” በሚል በቀረቡ 2 የትርጉም አቤቱታዎች ላይ ተጨማሪ ማጣራት ተደርጎባቸው ለውሳኔ በድጋሚ እንዲቀርቡ አቅጣጫ በማስቀመጥ በይደር ታልፈዋል።ከዚህ በተጨማሪም “ሕገ መንግሥታዊ ንብረት የማፍራት መብቴ ተጥሷል” በሚል ለጉባዔው በቀረበ 1 የንብረት ክርክር አቤቱታ ዙሪያ ጉባዔው ተጨማሪ ግልፀኝነት እና ማብራሪያ እንዲኖር ለማድረግ በተጠሪ መልስ እንዲሰጥበትና በድጋሚ ለውሳኔ እንዲቀርብ አዝዟል።በመጨረሻም ጉባዔው በዕለቱ ከተወያዬባቸው ጉዳዮች መካከል ፍትህ የማግኘት ሕገ መንግሥታዊ መብቴ ተጥሷል በሚል ከአዋጅ ቁጥር 47/67 ጋር ተያይዞ በመንግሥት የተወረሱ ቤቶችን በሚመለከት በቀረበለት የሕገ መንግሥት የትርጉም አቤቱታ ላይ ሰፊ ውይይት ካደረገ በኋላ ጉዳዩ በሕገ መንግሥቱ አንቀፅ 37(1) እንዲሁም አንቀፅ 9(1) ከተደነገጉ ጉዳዮች ጋር ይጣረሳል በሚል ትርጉም እንዲሰጥበት የውሳኔ ሐሳቡ ለፌዴሬሽን ም/ቤት እንዲላክ ወስኗል።See insights and adsBoost post

All reactions:4848