አጣሪ ጉባዔው በ50 የሕገ መንግሥት ትርጉም አቤቱታዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ ሰጠ።
March 27, 2024
“እያንዳንዱ ፈፃሚ እና አመራር የሚያስመሰግን ሥራ በመሥራት ተቋማዊ ለውጥ ለማምጣት መሥራት አለበት።” የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ ዋና ዳይሬክተር አቶ ደሳለኝ ወዬሳ።
June 4, 2024
Show all

አጣሪ ጉባዔው በ32 የሕገ መንግሥት የትርጉም አቤቱታዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ እና አቅጣጫ አስቀመጠ።

የኢፌዴሪ የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ ሐሙስ ግንቦት 8 ቀን 2016 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ በንዑስ አጣሪ ጉባዔ እና በአጣሪ ጉባዔ ጽ/ቤቱ የሕግ ተመራማሪዎች ሰፊ ማጣራት እና ምርመራ ተደርጎባቸው ለውሳኔ ከቀረቡለት አቤቱታዎች መካከል በ32ቱ ላይ ውሳኔ እና አቅጣጫ ሰጥቷል።

በዚህም 29 የሚሆኑ የትርጉም አቤቱታዎች ላይ ሕገ መንግሥታዊ ጥሰት አልተፈፀመባቸውም በሚል ውሳኔ የሰጠ ሲሆን ሌላ አንድ መዝገብ ላይ ተጨማሪ ማጣራት ተደርጎበት ለውሳኔ እንዲቀርብ ጉባዔው አቅጣጫ አስቀምጧል።

በሌላ በኩል  በሕጎች ሕገ መንግሥታዊነት ላይ በቀረበ ጉዳይ   የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር የኢፌዴሪ ሕገ መንግሥትን እና የትግራይ ክልል ሕገ መንግሥትን የሚቃረን አዲስ የመሸጋገሪያ ደንብ ቁጥር 4/2016 ወደ መደበኛ ሕግ ለመመለስ በሚል ያወጣ በመሆኑ ይህ ደንብ  የሕገ መንግሥቱን አንቀፆች 9(1)፣ 37፣ 55(5) እና አንቀጽ 80(3) ስሚጥስ ሕገ መንግሥታዊ አይደለም ተብሎ እንዲሻርልን በሚል ለጉባዔው የቀረበለትን አቤቱታ ጉባዔው የመረመረ ሲሆን በጉዳዩ ላይም ተጠሪ ምላሽ እንዲሰጥበት ትዕዛዝ ሰጥቷል። በመጨረሻም በዕለቱ በጉባዔው ከታዩ ጉዳዮች መካከል ከዚህ ቀደም መሰማት (public hearing) የተካሄደበት እና “የፌዴራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1234/2013 አንቀፅ 5 ንዑስ አንቀጽ 1 ፊደል ‘ሸ’ን ሕገ መንግሥታዊነት በተመለከተ የቀረበው የትርጉም አቤቱታ ሲሆን ጉባዔውም ” በጉዳዩ ላይ ሰፊ ውይይት በማድረግ ጉዳዩን በ2 አስተያየት በማዘጋጀት ለመጨረሻ ውሳኔ ወደ ፌዴሬሽን ም/ቤት እንዲላክ  ውሳኔ ተሰጥቶበታል።