አጣሪ ጉባዔው በስኬታማ ሩብ ዓመት አፈፃፀም
October 23, 2023
ጉባዔው በሁለት የአቤቱታ መዛግብት ላይ የሕገ መንግሥት ትርጉም ያስፈልጋቸዋል በማለት ውሳኔ አሳለፈ።
November 10, 2023
Show all

አጣሪ ጉባዔው በ126 የትርጉም አቤቱታዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ ሰጠ።

????????????????????????????????????

የኢፌዴሪ የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ ሐሙስ ጥቅምት 15 ቀን 2016 ዓ.ም  በነበረው ጉባዔ  በ126 የሕገ መንግሥት ትርጉም አቤቱታዎች ላይ ውሳኔ ሰጥቷል።

ጉባዔው ቀደም ሲል በጽ/ቤቱ የሕግ ባለሙያዎች፣ በዋና እና በንዑስ አጣሪ ጉባዔ ደረጃ ሰፊ ጥናትና ማጣራት በተደረገባቸው 126 የትርጉም አቤቱታ መዛግብት ላይ ተገቢውን ክርክር ካደረገ በኋላ ውሳኔ ሰጥቶባቸዋል።

በዚህም በዕለቱ ከቀረቡት 126 መዛግብት መካከል 122 የሚሆኑትን ምንም አይነት የሕገ መንግሥት ጥሰሰት ስላላገኘባቸው የሕገ መንግሥት ጥሰት የለባቸውም በሚል እንዲዘጉ የወሰነ ሲሆን ሌሎች ሁለት የአቤቱታ መዛግብት ላይ ተጨማሪ ማጣራት ተደርጎባቸው በድጋሚ ለውሳኔ እንዲቀርቡ ጉባዔው ሲወስን አንድ ጉዳይ ላይ በተጠሪ መልስ እንዲሰጥበት አቅጣጫ አሰቀምጧል።

በሌላ በኩል በዕለቱ የቀረበ አንድ የአቤቱታ መዝገብ አመልካች እና ተጠሪ በደረሱት ስምምነት መሠረት ተቋርጦ እንዲዘጋ ውሳኔ ተላልፏል።