የጉባዔ ጽ/ቤቱ አመራሮችና ሠራተኞች የሴቶችን ቀን አከበሩ።
March 27, 2024
አጣሪ ጉባዔው በ50 የሕገ መንግሥት ትርጉም አቤቱታዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ ሰጠ።
March 27, 2024
Show all

አጣሪ ጉባዔው በየጊዜው የተሻለ ሥራ እየሠራ መሆኑን ዕውቅና መስጠት እፈልጋለሁ ሲሉ የፌዴሬሽን ም/ቤት አፈ ጉባዔ የተከበሩ አቶ አገኘሁ ተሻገር ተናገሩ።

አርብ መጋቢት 6 ቀን 2016 ዓ.ምየኢፌዴሪ የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ በአሠራር ስነ ሥርዓት ረቂቁ ላይ ከፌዴሬሽን ም/ቤት ጋር ውይይት አደረገ።በውይይቱ ላይ የፌዴሬሽን ም/ቤት አፈ ጉባዔ የተከበሩ አቶ አገኘሁ ተሻገር የተገኙ ሲሆን አጣሪ ጉባዔው በየጊዜው ላሳየው መሻሻል ዕውቅና ሰጥተዋል። አፈ ጉባዔው በተጨማሪም ጉባዔው የሕጎችን ሕገ መንግሥታዊነት ማጣራት ላይ በትኩረት እንዲሠራ አሳስበዋል።በዕለቱ መድረኩን የመሩት የፌዴራል ጠ/ፍ/ቤት ፕሬዝዳንት እና የአጣሪ ጉባዔው ሰብሳቢ ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት በበኩላቸው የአሠራር ሥነ ሥርዓቱ የዜጎችን ሕገ መንግሥታዊ ጥያቄ በፍጥነት ለመፍታት እንደሚያስችል ገልፀው የአሠራር ሥነ ሥርዓት ረቂቁ በሕገ መንግሥቱ አንቀፅ 84(4) መሠረት በፌዴሬሽን ም/ቤት በቀጣይ ግንቦት በሚደረገው ስብሰባ እንዲፀድቅ ጥሪ አቅርበዋል።የመድረኩ ተሳታፊዎችም የተለያዩ ጥያቄዎችን፤ ለግብዓት የሚሆኑ ሐሳቦችን እንዲሁም ውይይት እና ውሳኔ የሚጠይቁ ሐሳቦችን በሰፊው አንስተው ውይይት እና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል።ረቂቅ የአሠራር ሥነ ስርዓቱ ከዚህ በፊት ለባለድርሻ አካላት ቀርቦ ውይይት የተደረገበት ሲሆን፤ ቀጣይም ለውሳኔ ከመቅረቡ በፊት በጉባዔ አባላቱ እና በቋሚ ኮሚቴዎች መካከል አንድ የመጨረሻ ውይይት እንዲደረግበት የተከበሩ አቶ አገኘሁ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።የኢፌዴሪ የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ በሕገ መንግሥቱ አንቀፅ 82(1) መሠረት የተቋቋመ እና ሕገ መንግሥታዊ ጉዳዮችን የማጣራት ሥልጣን ያለው ተቋም ሲሆን፤ የሚቀርቡለትን ሕገ መንግሥታዊ ጥያቄዎች በመመርመር ሕገ መንግሥታዊ ጥሰት የለበትም ብሎ ካመነ ውሳኔውን ለአቤቱታ አቅራቢው የሚያሳውቅ ሲሆን ውሳኔው ሕገ መንግሥታዊ ጥሰት ተፈፅሞበታል ብሎ ሲያምን ደግሞ የውሳኔ ሐሳቡን ለፌዴሬሽን ም/ቤት እንደሚልክ ይታወቃል።