ጉባዔው በ 86 ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ
August 7, 2023
ጉባዔው በ71 የሕገ መንግሥት ትርጉም አቤቱታዎች ላይ ውሳኔ ሰጠ።
September 13, 2023
Show all

አጣሪ ጉባዔው በበጀት ዓመት ዕቅዱ ላይ ውይይት አደረገ።

????????????????????????????????????

ጳጉሜ 3 ቀን 2015 ዓ.ም (አዲስ አበባ)

የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ በ2016 በጀት ዓመት ዕቅዱ ላይ ጳጉሜ 2 ቀን 2015 ዓ.ም ውይይት አካሂዷል።

አጣሪ ጉባዔው ሥራ ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ ከ8ሺ በላይ አቤቱታዎች ቀርበውለት ከ4ሺ በላይ የሆኑት ውሳኔ ማግኘታቸውን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ደሳለኝ ወዬሳ ተናግረዋል። ከዚህ ጋር በተያያዘ ከ3750 በላይ የአቤቱታ መዛግብት ወደ 2016 በጀት ዓመት መተላለፋቸውን የገለፁት ኃላፊው፤ ጉዳዩን ለማቃለል የዘመቻ ሥራ እና ከመደበኛ የሥራ ሰዓት ውጭ በሚደረጉ ሥራዎች የተከማቹ የአቤቱታ መዛግብትን ምላሽ ለመሥጠት እየተሠራበት እንደሚገኝ አስረድተዋል። በዚህም ከመደበኛ የሥራ ሰዓት ውጭ በዘመቻ እና አምሽቶ በመሥራት የዜጎችን ሕገ መንግሥታዊ ጥያቄ ለመመለስ በሚደረገው ዘመቻ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ እየሠሩ ለሚገኙት የጉባዔው አባላት እና ለሠራተኞቹ ኃላፊው ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

በሌላ በኩል ባሳለፍነው 2015 በጀት ዓመት ከቀረቡት 847የሕገ መንግሥት ትርጉም አቤቱታዎች መካከል 793 የሚሆኑት በጉባዔው ታይተው 5 አቤቱታዎች ትርጉም እንዲሰጥባቸው ወደ ፌዴሬሽን ም/ቤት የተላኩ ሲሆን ነገር ግን  በ2014 በጀት ዓመት በነበረው “የተጠሪ ምላሽ ይካተት” የሚል አዲስ አሠራር አንድም መዝገብ ወደ ፌዴሬሽን ም/ቤት እንዳልተላከ በሪፖርቱ ተመላክቷል።

በቀረበው እቅድና ሪፖርት ላይ የአጣሪ ጉባዔው አባላት እና ሰብሳቢዎች ሐሳብና አስተያዬታቸውን የሰጡ ሲሆን፤ የንዑስ ጉባዔ አባላት አንድ ተጨማሪ ቡድን በማቋቋም በ2 መልኩ ተደራጅተው በአዲስ መልክ የሚቀርቡትንና የቆዩ አቤቱታዎችን ጎን ለጎን እንዲሠሩ የሚል ሐሳብ የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔው ሰብሳቢ  ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት አቅርበዋል።

ከዚህ በተጨማሪም በበጀት ዓመቱ በሀገራዊ እና መሠረታዊ ጉዳዮች ላይ እስከ አሥር የሚደርሱ  የመሰማት መድረኮች እንዲደረጉ እንዲሁም የዜጎች መብት እንዲከበር እና የመንግሥት ስልጣን በሕገ መንግሥቱ መሰረት መሥራት እንደሚገባ የጉባዔ አባላቱ አስተያዬት ሰጥተዋል።

በመጨረሻም ጥራት እና ብዛት ያለው ሥራ ለመሥራት የባለሙያዎችን አቅም ግንባታ መሥራት እንደሚገባ እንዲሁም አቤቱታ አቅራቢዎች በቴክኖሎጅ ካሉበት ቦታ ሆነው ጉዳያቸውን የሚያቀርቡበት እና ምላሽ የሚያገኙበት ዘዴ እንዲዘጋጅ የጉባዔ አባላቱ ያሳሰቡ ሲሆን የሕዝብ ግንኙነት እና ማስተማር  እንዲሁም መረጃ የማድረስ ሥራው በሁሉም የግንኙነት አግባቦች በትኩረት እንዲሠራበት ሲሉ ሐሳባቸውን ሰጥተዋል።