የሕገመንግስት ትርጉም የሚቀርብ አቤቱታ ይዘት

  1. ለአጣሪ ጉባኤው በሚቀርብ አንድ አቤቱታ ሊካተቱ የሚገባቸው ነጥቦች፡-
  • ሀ. የጉባኤውን ስምና አድራሻ
  • ለ. የአመልካች /አቤቱታ አቅራቢው/ሙሉ ስምና አድራሻ ስልክ ቁጥር
  • ሐ. የተጠሪ  ሙሉ ስምና አድራሻ
  • መ. የአቤቱታው ርእስ
  • ሠ. ግልጽና አጭር የሆነ  ህገ መንግስታዊ መብት ጥሰቱን የሚያሳይ አቤቱታ
  • ረ. የተጣሰውን ሕጋዊ መብት፣ ሕጋዊ ጥቅም ወይም ሕጋዊ ስልጣን እና ይሄው ከህገ መንግስቱ ድንጋጌ ጋር የሚጋጭበት ምክንያት ሊያጠቃልል ይገባል
  • ሰ. በውክልና ለሚቀርብ አቤቱታ በውክልና የቀረበ መሆኑን የሚገልጽ መሆን አለበት
  • ሸ.ጉዳዩ የመጨረሻ ውሳኔ ያገኘ መሆን መጠቀስ አለበት
  • ቀ. የአቤቱታውንና አባሪ ትርጉም የተጠየቀባቸው ውሳኔዎች ማስረጃዎች አደረጃጀት እንደዚሁም የገጽ ብዛት የያዘ መግለጫ
  1. ከላይ የተዘረዘሩት እንደተጠበቀ ሁኖ
  • ሀ. ትርጉም የተጠየቀበት ሕግ በሆነ ጊዜ የሕጉ አጭር ርዕስ፣ ቁጥር ፣   የታተመበት ቀን፣ ዓመተ ምህረት እና ድንጋጌ
  • ለ. ትርጉም የተጠየቀበት የመንግስት አካል ወይም የባለስልጣን ውሳኔ በሆነ ጊዜ ለመጨረሻው ውሳኔ ምክንያት የሆኑ ሌሎች ውሳኔዎች በቅደም ተከተል፣ የመጨረሻው ውሳኔ፣ ውሳኔውን የሰጠው አካል፣ ውሳኔ/ውሳኔዎቹ የተሰጠበት/ጡበት ቀን እና ዓ.ም ሊይዝ ይገባል
  • ሐ. ትርጉም የተጠየቀበት ውሳኔ ከፍርድ ቤት፣ ከሌሎች የዳኝነት ስልጣን ካላቸው አካላት የሚላክ የህገ መንግስት ትርጉም ጥያቄ እንደ አግባብነታቸው ከላይ የተጠቀሱትን ዝርዝር ጉዳዮች ሊይዝ ይገባል
  1. ከአቤቱታው ጋር ተያይዘው የሚቀርቡ አባሪዎችም፡-
  • ሀ. ለትርጉም ጥያቄው መነሻ የሆነው የፍ/ቤት  ውሳኔ  በሆነ ጊዜ በየደረጃው ያሉ ፍ/ቤቶች የሰጡት ውሳኔዎች ብቻ ይያያዛሉ
  • ለ. ለትርጉም ጥያቄው መነሻ የሆነው የባለስልጣን ውሳኔ በሆነ ጊዜ በየደረጃው የተሰጡት የባለስልጣን ውሳኔዎች ብቻ ይያያዛሉ
  • ሐ. ሕገ መንግታዊ መብቴ ተጥሷል ወይም አልተከበረም በሚል ሕገ መንግስታዊ አቤቱታውን በቀጥታ የሚያቀርብ ሰው ይህንኑ ያረጋግጡልኛል ያላቸውን ማስረጃዎች ወይም ጥሰቱን የሚያመለክት የማስረጃውን ክፍል ብቻ አያይዞ ሊያቀርብ ይችላል፡፡
  • መ. በውክልና ለሚቀርብ አቤቱታ የውክልና ስልጣን የሚገልጽ ሰነድ
  1. ለሕገ መንግስት ትርጉም የሚቀርብ አቤቱታ በፌዴራል መንግስቱ የሥራ ቋንቋ ተዘጋጅቶ ሊቀርብ ይገባል፡፡ ከፌዴራል መንግስቱ የስራ ቋንቋ ውጭ የሆነ ይዘት ያላቸው ውሳኔዎች እና አባሪ ማስረጃዎች በፌዴራሉ መንግስት የሥራ ቋንቋ ተተርጉመው እና ተረጋግጠው ሊቀርቡ ይገባል፡፡