ስድስተኛው ሀገራዊ ምርጫ በሚመለከት በቀረበ የሕገ መንግስት ትርጉም ጥያቄ ሂደት ላይ ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጠ
May 14, 2020
ጉባዔው ሕገ መንግሥቱ ሲረቅና ሲፀድቅ ተሳትፈው የነበሩ አካላትን አስተያየት አዳመጠ
May 20, 2020

“አሁን ያለንበትን ወቅት የሕገ መንግሥት ጊዜ በማለት ልንጠራው እንችላለን” ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ

“አሁን ያለንበትን ወቅት የሕገ መንግሥት ጊዜ በማለት ልንጠራው እንችላለን”
ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ


የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ ከ6ኛው ዙር ብሔራዊ ምርጫ ጋር ተያይዞ በቀረበው የሕገ መንግሥት ትርጉም ጥያቄ ላይ ዛሬ ግንቦት 08/2012 የባለሙያዎችን ሀሳብ የማድመጥ ስነ ስርዓት (hearing) አካሄደ።
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከ6ኛው ዙር ሀገራዊ ምርጫ ጋር ተያይዞ ለሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ ባቀረበው የሕገ መንግሥት ትርጉም ጥያቄ ላይ በአዋጅ ቁጥር 798/2005 አንቀጽ 9 ላይ አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው በሚያጣራው ጉዳይ ላይ የሚመለከተውን አካል አስተያየት መቀበል እንደሚችል በተዘረዘረው መሠረት፣ የባለሙያዎችን ሀሳብ ለመስማት የያዘውን ፕሮግራም የመጀመሪያ ክፍል ዛሬ ግንቦት 08/2012 በሸራተን አዲስ ሆቴል መድረክ በመፍጠር በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር ከሚኖሩ ለጉዳዩ ቅርበት ካላቸው ባለሙያዎች ሀሳብ የማድመጥ ስነ ስርዓት (hearing) አካሂዷል።
የጉባዔው ሰብሳቢ ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ በስነ ስርዓቱ ማስጀመሪያ ላይ ባደረጉት ንግግር አሁን ያለንበትን ወቅት “የሕገ መንግሥት ጊዜ” በማለት ልንጠራው እንችላለን ሲሉ ገልጸውታል። አሀን ባለንበት ወቅት በሕገ መንግሥቱ ዙሪያ ከተለያዩ አቅጣጫዎች የሚነሱት ጥያቄዎች አቀራረባቸው የተለያየ ቢሆንም ለሕግ በመቆም ሕግን የመከላከል ተግባር በመሆኑ በአዎንታዊ ጎኑ ሊታዩ እንደሚገባ ተናግረዋል። በተጨማሪም ይህ ወቅት ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓትን ለማስፈን ጥሩ አጋጣሚን የፈጠረ ነው ሲሉም ተናግረዋል።
በመድረኩ ላይ የሕገ መንግሥት ምሁራን ሀሳባቸውን ያቀረቡና ውይይት የተደረገባቸው ሲሆን፣ በመጀመሪያ ሀሳባቸውን ያቀረቡት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሕግ መምህር የሆኑት ዶ/ር ጌታቸው አሰፋ ሲሆኑ በመነሻቸውም ከቀረቡት አማራጮች መካከል የሕገ መንግሥት ትርጉም የሚለው መመረጡ ተገቢ ነው በሚል ሀሳባቸውን አቅርበዋል። ለዚህም ምክንያታቸውን ሲያስረዱ በሕገ መንግሥቱ በቀጥታ መልስ የሌላቸው ጉዳዮች ሲገጥሙ የሚሸፈኑት በትርጉም ስርዓት መሆኑን ጠቁመዋል።
የሕገ መንግሥት ክፍተት ሲፈጠር ሕገ መንግሥትን ማሻሻል አንዱ ዘዴ መሆኑን ጠቁመው፣ ነገር ግን ይህ የሚደረገው በሕገ መንግሥቱ ላይ አዲስ ሀሳብ ለመጨመር ወይም ከወቅቱ ሁኔታ ጋር የማይሄድና አስፈላጊ አይደለም ተብሎ የሚታሰብ ሀሳብ ከሕገ መንግሥቱ ለመቀነስ ሲፈለግ የሚከወን በመሆኑ አሁን ለተከሰተው ጉዳይ ተመራጭ አለመሆኑን ተናግረዋል። የሕገ መንግሥት ትርጉም ግን ተዛማጅ ሃሳቦች ሕገ መንግሥቱ ውስጥ ተካተው ነገር ግን በቀጥታ የማይመልሱ ሲሆኑ የሚመረጥ መሆኑን አክለው ገልጸዋል።
በመቀጠልም በአራት የሕግ ምሁራን የተዘጋጀ ሀሳብ መሆኑን የገለጹት ዶ/ር ሠለሞን አየለ በፅሑፍ ያዘጋጁትን ሀሳብ አቅርበዋል። እሳቸውም ጉዳዩ ለሕገ መንግሥት ትርጉም መቅረቡን በመደገፍ፣ በዚህ መልኩ ለሕዝብ ግልጽ በሆነ መድረክ ጉዳዩ ለውይይት መቅረቡ የሕገ መንግሥት ባህልን በጠንካራ መሰረት ላይ የሚያስቀምጥና የሚያስመሰግን ነው ብለዋል።
ከሁለቱ ሀሳብ አቅራቢዎች በኋላ የጉባዔ አባላት የተለያዩ ጥያቄዎችን ያነሱ ሲሆን ከጥያቄዎቹም መካከል “አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የሚያሳውጅ ክስተት ሲፈጠር ምርጫን በማራዘም ዙሪያ የሀገራት ተነፃፃሪ ተሞክሮ ምን ይመስላል፣ ኪቪድ 19ን ለመከላከል አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መታወጁ ግድ ነው ወይ፣ አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ሲነሳ ምርጫን በምን ያህል ጊዜ ማድረግ ይቻላል፣ በምርጫ ካልሆነ የመንግሥትን ሥልጣን መያዝ እንደማይቻል በሕገ መንግሥቱ ተደንግጎ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ምክንያት ደግሞ የመንግሥት የሥልጣን ጊዜ የሚራዘም ከሆ