ጉባዔው ሁለት መዝገቦችን ለሕገ መንግሥት ትርጉም ወደ ፌ/ም/ቤት ላከ
February 13, 2020
በሕገ መንግሥቱ አንቀፅ 40/1 የተደነገገ መብትን ጥሶ የተገኘ መዝገብ ለትርጉም ወደ ፌዴሬሽን ምክር ቤት ተላከ
February 27, 2020

በጉባዔው ም/ሰብሳቢ ክቡር አቶ ሠለሞን አረዳ የተመራው የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ ልዑካን ቡድን ጀርመን በርሊን የልምድ ልውውጥ አካሄደ

በጉባዔው ም/ሰብሳቢ ክቡር አቶ ሠለሞን አረዳ የተመራው የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ ልዑካን ቡድን ጀርመን በርሊን የልምድ ልውውጥ አካሄደ

የአጣሪ ጉባዔው ልዑካን ቡድን “የሕግ የበላይነት፣ ፍትህና ልማት” (Rule of Law, Justice & Development) በሚል ርዕሰ ጉዳይ በጀርመን ሀገር በርሊን ከተማ ከጃንዋሪ 26 እስከ 28/2020 በተካሄደ ሥልጠና ላይ ተሳትፎ የልምድ ልውውጥ አከናወነ፡፡

ለነፃ የዳኝነት ስርዓት ተቋማዊ መዋቅርን ማጠናከር (Strengthening Institutional Structure for an Independent Judiciary) በሚል ርዕስ የተለያዩ ጥናታዊ ፅሑፎች ቀርበው ውይይት የተደረገባቸው መሆኑን የአጣሪ ጉባዔው ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ደሳለኝ ወዬሳ ገልፀዋል፡፡ የተለያዩ ሀገራት ልምድ በቀረበበት በዚሁ ሥልጠና ላይ በካሪቢያን ፍርድ ቤቶች ፕሬዚደንት የተከበሩ አድሪያን ሳውንደርስ የካሪቢያን ሀገራት ልምድ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡ በዚሁ መሰረት በተከበሩ አድሪያን ለታዳሚው ካቀረቡት ሀሳቦች መካከል የፍርድ ቤቶች እና በብቃት ላይ የተመሰረተ የዳኞች አሿሿም ነፃነት፣ ለፍርድ ቤቶች በቂ በጀት መመደብን የተመለከተ እንዲሁም የዳኞች የሥነ ምግባር ደንብና የመሣሰሉት ላይ ተመርኩዘው ባቀረቡት ፅሑፍ ውይይት ተደርጎ የልምድ ልውውጥ መከናወኑን አቶ ደሳለኝ ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም በ“ፍርድ ቤቶች ሊያጋጥሙ ስለሚችሉ የሙስና ስጋቶች”፣ “የኢንተርኔት እና ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ሙስናን ለመታገል”፣ “የኢንፎርሜሽንና ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ እና በአጠቃላይ የማኅበራዊ ድረ-ገፆችን በመጠቀም በፍትህ ስርዓቱ ላይ ግልፅነትን መፍጠር” እንዲሁም “ሥርዓተ ፆታና የዳኝነት ልዕልና” በሚሉ ርዕሶችና በመሳሰሉ ሌሎች ርዕሶች ላይ በተለያዩ አቅራቢዎች የሥልጠና ፅሑፎች ቀርበው ሰፊ ውይይት ተደርጎባቸው ልምድ የተቀሰመባቸው መሆኑን የልዑካን ቡድኑ አባል በመሆን ተጉዘው የነበሩት አቶ ደሳለኝ ተናግረዋል፡፡ በኢትዮጵያም በኩል የልዑካን ቡድኑን የመሩት ክቡር አቶ ሰለሞን አረዳ በሀገራችን አሠራር ላይ ለታዳሚው ገለጻ አድርገዋል።

አቶ ደሳለኝ አያይዘው እንደተናገሩት እንዲህ ዓይነት ዓለም አቀፍ መድረኮች ላይ የሀገራችን ተሳትፎ እየተጠናከረ መሄዱ ለሀገራችን የፍትህ ሥርዓት መጎልበት ትልቅ አስተዋፅኦ ይኖረዋል በማለት ገልፀዋል፡፡