የመጀመሪያው የአፍሪካ እንስት ዳኞች ጉባዔ በጋቦን ሊብረቪሌ እ.ኤ.አ ከግንቦት 2 እስከ 6 ቀን 2023 ተካሄደ።
May 10, 2023
ጉባዔው በ11 ሕገ መንግሥታዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ
May 19, 2023

ሴንት ፒትርስበርግ በተካሄደው የአለምአቀፍ ስብሰባ ኢትዮጵያ ልምዷን አካፈለች

ሕገ መንግሥትና ሕገ መንግሥታዊ ጥበቃ፤ የሕግና የሕገ መንግሥታዊ መርሆችን ማሳደግና ማጎልበት በሚል ርእስ በሩስያ ሴንት ፒትርስበርግ ከግንቦት 10-13 2023 በተካሄደው አለምአቀፍ ስብሰባ ኢትዮጵያን ጨምሮ የተለያዩ ሀገራት ልምዳቸውን አካፈሉ፡፡

በዚህ ስብሰባ ኢትዮጵያን በመወከል የኢትዮጵያን የሕገ መንግሥት ታሪክና የሕገ መንግሥት አተረጓጎም ስርአትን  በፅሁፍ ያቀረቡት የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዚዳንትና የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ ሰብሰቢ ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት በኢትዮጵያ የተፃፈ ሕገ መንግሥት የተጀመረው እ ኤ አ በ1931 ዓ.ም እንደሆነና አሱን ተከትሎም በ1955፣ በ1974፣ በ1987 እና በ991 የፀደቀውንና አሁን እየተቀምንበት ያለውን ጨምሮ አምስት የተፃፉ ሕገ መንግሥቶች እንዳሏት ገልፀዋል፡፡ አያይዘውም የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሕገ መንግሥት አወቃርንና የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ የሕገ መንግሥት ትርጉምን አስመልክቶ በሕገ መንግሥቱ የተሰጠውን ድርሻ ሲያብራሩ  የመጨረሻ ውሳኔ የሚሰጠው የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የፌዴሬሽን ም/ቤት ሕግ ተርጓሚ አካል ባለመሆኑ የሕገ መንግሥት ጉዳዮችን ለማጣራት የሕግ ባለሙያዎችን የያዘ አጣሪ ጉባዔ መቋቋሙን አስረድተዋል፡፡

የሕገ መንግሥት አጣሪ ጉባዔውን አወቃቀር በተመለከተ ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ሲናገሩ አጣሪ ጉባዔው በሕገ መንግሥቱ አንቀፅ 82 መሰረት የተቋቋመና የጠቅላይ ፍ/ቤትን ፕሬዚዳንትና ም/ፕሬዚዳንትን ጨምሮ 11 አባላት ያሉት እንደሆነ፣ ከነዚህ ውስጥ ሶስቱ ከፌዴሬሽን ም/ቤት የሚወከሉ፣ ስድስቱ ደግሞ በሙያዊ ብቃታቸውና በባህሪያቸው ተመርጠው በኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት አማካኝነት የሚሾሙ እንደሆኑ አብራርተዋል፡፡ አጣሪ ጉባዔው በሕገ መንግሥት ትርጉም ያለውን ድርሻ በተመለከተ ጉባዔው የቀረቡለትን የሕገ መንግሥት አቤቱታዎችን በማጣራት የሕገ መንግሥት ትርጉም ያስፈልገዋል ሲል የውሳኔ ሀሳቡን ለኢ.ፌ.ዴ.ሪ የፌዴሬሽን ም/ቤት ሲያቀርብ፣ የሕገ መንግሥት ትርጉም አያስፈልገውም ሲል ግን ውሳኔውን ለባለጉዳዩ እንደሚያሳውቅ ገልፀዋል፡፡

እስካሁን የታዩ ሕገ መንግሥታዊ ጉዳዮችንም በተመለከተ በአብዛኛው የፍ/ቤትን የመጨረሻ ውሳኔ በመቃወም የቀረቡ ሲሆኑ ጥቂቶቹ ደግሞ የአስተዳደራዊ ተቋማት ውሳኔን በመቃወም የቀረቡ እንደሆኑ አመልክተዋል፡፡