የሴቶች ወቶችና ህፃናት ዳይሬክቶሬት ተግባርና ኃላፊነት
- የሴቶችና ወጣቶችን እኩል ተሳታፊነትና ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ፣ እንዲሁም የህጻናት በመብትና ደህንነት ለማስጠቅ የሚያስችል ለሴክተሩ ተጠሪ በሆኑ ተቋማት የአሰራር ሥርዓት መዘርጋት
- የሴቶችንና የወጣቶችን ተሳታፊነትና ተጠቃሚነትን ለማሳደግና የህጻናት መብትና ደህንነት ለማረጋገጥ እና የህጻናትን ተሳትፎ ለማሳደግ የባለድርሻ አካላትን አቅም ማጐልበት
- የማካተቻውን ተግባራዊነት በየ6 ወሩ በመገምገም ለሚመለከተው አካል ሪፖርት ማቅረብ፣
- በተቋሙ የሥርዓተ-ፆታን ክፍተት ለመሙላት የአቅም ግንባታ ሥራዎችን ማከናወንና የሴቶችንና ወጣቶችን ማብቃት
- የተቋሙ የስራ ሂደቶች ሥርዓተ-ፆታን በእቅድ ዝግጅት፣ አፈፃፀም ክትትልና ግምገማ አካተው ተግባራዊ ማድረጋቸውን ለማረጋገጥ የሚያስችል የክትትልና ድጋፍ ሥርዓት በመዘርጋት ተፈጻሚ ማድረግ፣
- በፆታ የተተነተነ መረጃ አደራጅቶ መያዝ፣
- በአፈጻጸም ሂደት የተገኙ ግብዓቶችን በማሰባሰብ ማካተቻውን እንዳስፈላጊነቱ ማሻሻል፣