ጉባዔው ከሕገ መንግሥት አተረጓጎም ጋር በተያያዘ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ጠቅላይ ፍ/ቤት ዳኞች ጋር የግንዛቤ ማስጨበጫ ውይይት አካሄደ
March 17, 2020
የፕሬስ መግለጫ የህገ መንግስት አጣሪ ጉባዔ
May 12, 2020

   ማስታወቂያ

   ማስታወቂያ

 

የኮሮና  ቫይረስ ( COVID 19) ከጥቂት ቀናት በፊት አለም አቀፍ ወረርሽኝ ተብሎ በአለም ጤና ድርጅት መታወጁ ይታወቃል፡፡ ይህ ወረርሽኝ በሀገራችንም ባአስራ ሁለት ሰዎች ላይ መገኘቱን መንግስት አስታውቋል፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ ወረርሽኙ በከፍተኛ ደረጃ የሚሰራጨው በንክኪ መሆኑ አንፃር ሰዎች በብዛት በሚገኙበት አካባቢ ለቫይረሱ  ስርጭት ከፍተኛ ሚና ያለው በመሆኑ መንግስት ት/ት ቤቶችንና  በርካታ ህዝብ በአንድ ላይ የሚሰበስቡ ስብሰባዎችን ለ15 ቀናት እንዳይካሄዱ፣ ከተለዩ የስራ ዘርፎች ውጭ ያሉ የመንግስት ሰራተኞችም በቤታቸው ሆነው ስራቸውን እንዲሰሩ መልእክት ማስተላለፉ ይታወቃል፡፡

በመሆኑም የሕገ መንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ ፅ/ቤት ሬጅስትራር በየእለቱ በርካታ ባለጉዳዮችን የሚያስተናግድ ከመሆኑ አንፃር የቫይረሱን ስርጭት ለመከላከል አዳዲስ መዝገቦችን ከመክፈትና ማንኛውም ከባለጉዳይ ጋር በአካል የሚደረጉ ውይይቶችን ላልተወሰኑ ቀናት የማናስተናግድ መሆኑን እየጠቆምን አቤቱታ አቅራቢዎች አቤቱታችሁን በተሟላ መልኩ በሶፍት ኮፒ በማደራጀት በዌብሳይታችን /www.cci.gov.et/ ላይ በሚገኘው አቤቱታ ማቅረቢያ ቅፅ ላይ ሞልታችሁ መላክ እንደምትችሉ እናሳውቃለን፡፡

አቤቱታ ማቅረቢያ

የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል በመንግስትና በጤና ባለሙያዎች የሚወጡትን መመሪያዎች በመጠበቅና በመተግበር ሃላፊታችንን እንወጣ!

 

የሕገ መንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ ፅ/ቤት