የሕገ መንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ ጽ/ቤት ለፌደሬሽን ምክር ቤት አባላት ስልጠና ሰጠ
October 10, 2019
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ አዲስ ሶፍት ዌር ከቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ተረከበ
December 2, 2019

ለቃሊቲ ኮንስትራክሽን ዕቃዎች ማምረቻ ፋብሪካ ሴት ሰራተኞች በሴቶች መብቶች ዙሪያ ስልጠና ተሰጠ

ለቃሊቲ ኮንስትራክሽን ዕቃዎች ማምረቻ ፋብሪካ ሴት ሰራተኞች በሴቶች መብቶች ዙሪያ ስልጠና ተሰጠ

የሕገ መንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ ጽ/ቤት ህዳር 9 ቀን 2012 ዓ.ም የሴቶች መብት በኢ.ፌ.ዴ.ሬ ሕገ መንግስት በሚል ርዕስ ለቃሊቲ ኮንስትራክሽን ዕቃዎች ማምረቻ ፋብሪካ ሴት ሰራተኞች ሰልጠና ሰጠ፡፡

በሕገ መንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ ጽ/ቤት የሴቶች ፣ ህጻናትና ወጣቶች ዳይሬክቶሬት እና በህገ መንግስት አስተምህሮ ክፍል አማካይነት በፋብሪካው ቅጥር ግቢ በተዘጋጀው ስልጠና የፋብሪካው ሴት ሰራተኞችና አመራሮች በስልጠናው ላይ ተሳትፈዋል፡፡

በስልጠናው መክፈቻ ላይ የቃሊቲ ኮንስትራክሽን ዕቃዎች ማምረቻ ፋብሪካ የፋብሪካ ሥራ አስኪያጅ አቶ ዋጋዬ ተፈራ የሕገ መንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ ጽ/ቤት ይህን የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መስጠቱን አመስግነው የተቋሙ ሴት ሰራተኞች ከዚህ መድረክ በተለይ የሴቶቸ መብቶችን በተገቢው ተገንዝበው ሴቶች መብትና ግዴታቸውን በማወቅ የዕለት ተዕለት ስራቸውን ለማከናወን እንደሚረዳቸው አስታውቀዋል፡፡ በተለይ የፋብሪካው ሰራተኞች ሕገ መንግስታዊ መብታቸው አስከምን ድረስ እንደሆነ ተረድተውና በቂ ዕውቀት አግኝተው የተቋሙን ርዕይና ተልዕኮ ለማሳካት የጎላ አስተዋጽኦ እንደሚኖራቸው ገልጸዋል፡፡

????????????????????????????????????

የስልጠናውን ጽሁፍ ያቀረቡት የሕገ መንግስት አስተምህሮ ቡድን መሪ አቶ ያደታ ግዛው ሴቶች እ.ኤ.አ ከ1908 ጀምሮ ትግል ሲያካሂዱ የቆዩ ሲሆን በሴቶች ዙሪያ አለም አቀፍ ስምምነቶቸ ከመጽደቃቸው ባሻገር በተባበሩት መንግስታት እ.ኤ.አ በ1948 በሴቶች ዙሪያ የሚሰራ አንድ ኮሚሽን እንዲቋቋም መደረጉን ተናግረዋል፡፡
ይህ ኮሚሽን ከ184 አገራት በላይ ተቀባይነት ያገኘና በሴቶች ዙሪያ ላይ የተፈረሙ ስምምነቶችን ያጸደቀ ሲሆን ሴቶች የእኩልነት መብታቸውን በማስከበር ረገድ በከፍተኛ ደረጃ የበኩሉን ድርሻ ተወጥቷል ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያም ስምምነቶቹን ከማጽደቅ ባሻገር ከሽግግር መንግስት ጊዜ ጀምሮ የሴቶች ፖሊሲ በመቅረጽና ፖሊሲውን መሰረት በማድረግ የ1987 ዓ.ም የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሕገ መንግስት ውስጥ በተለይ በአንቀጽ 35 ላይ እንዲካተት ያደረገች ሲሆን ሌሎች የህግ ማዕቀፎች ወጥተው በሴቶች መብቶች ዙሪያ ከፍተኛ ስራ ለመስራት ጥረት የተደረገበት ሁኔታ እንዳለ አመልክተዋል፡፡

በቀረበው ጽሁፍና ማብራሪያ ላይ ከሴቶችና ከሕገ መንግስቱ አንጻር እንዲሁም ከሕገ መንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ ተቋም ጋር በተያያዘ አስተያየቶችና ጥያቄዎች ቀርበው አቶ ያደታ ግዛውና ወ/ሮ አስቴር ተሰማ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

ስልጠናውን የተካፈሉ የፋብሪካው ሰራተኞችም እንደዚህ ዓይነቱ ስልጠና በቀጣይ ተጠናከሮ ሴቶችና ሌሎች ሰራተኞች የግንዛቤ አድማሳቸውን የሚያሰፉበት ሁኔታ እንዲፈጠር የሕገ መንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ ጽ/ቤት ትብብሩን ሊያጠናክር ይገባል ሲሉ ተናግረዋል፡፡