በሕገ መንግሥቱ አንቀፅ 40/1 የተደነገገ መብትን ጥሶ የተገኘ መዝገብ ለትርጉም ወደ ፌዴሬሽን ምክር ቤት ተላከ
February 27, 2020
ማርች 8
March 6, 2020

ለመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት ሴት ሠራተኞች በሕገ መንግሥቱ በተደነገጉ የሴቶች መብቶች ላይ የግማሽ ቀን ሥልጠና ተሰጠ

????????????????????????????????????

ለመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት ሴት ሠራተኞች በሕገ መንግሥቱ በተደነገጉ የሴቶች መብቶች ላይ የግማሽ ቀን ሥልጠና ተሰጠ

የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ በጽ/ቤቱ የሕገ መንግሥት ጥናት ባለሙያዎች አማካይነት ለመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት ሴት ሠራተኞች በሕገ መንግሥቱ በተደነገጉ የሴቶች መብቶች ላይ በድርጅቱ አዳራሽ የግማሽ ቀን ሥልጠና ሰጠ፡፡

ሥልጠናው የተዘጋጀው በጉባዔው ጽ/ቤት የሴቶች፣ ህጻናትና ወጣቶች ዳይሬክቶሬት አማካይነት ሲሆን፣ ሥልጠናውን በቦታው በመገኘት የሰጡት በጽ/ቤቱ የሕገ መንግሥት ከፍተኛ ተመራማሪ በሆኑት አቶ ከላሊ ኪሮስ እና በጥናትና ምርምር ዳይሬክቶሬት ቡድን መሪ በሆኑት አቶ ያደታ ግዛው ናቸው፡፡ አቶ ከላሊ የሴቶች መብትን አስመልክቶ ሀገራችን ፈርማ የሕጓ አካል ያደረገቻቸው ዓለም አቀፍ ድንጋጌዎች እንዲሁም ከንጉሡ ጊዜ ጀምሮ የነበሩ የሀገራችን ሕገ መንግሥታት የሴቶች መብትን በምን ዓይነት መልኩ አካተውት እንደነበረ ያብራሩ ሲሆን፣ በማስከተልም የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሕገ መንግሥት ለሴቶች መብት የሰጠውን ቦታ በስፋት በማንሳት ለታዳሚያኑ አቅርበዋል፡፡

አቶ ያደታ በበኩላቸው ለአጣሪ ጉባዔው ከቀረቡ መዝገቦች መካከል ከሴቶች መብት ጋር ተያይዞ የሕገ መንግሥት ትርጉም የተሰጠባቸው መዝገቦችን በማቅረብ ከሠልጣኞቹ የተለያዩ ሀሳቦችና ጥያቄዎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡

የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ ሕገ መንግሥታዊ አቤቱታዎች ሲቀርቡለት እንዲያጣራ በሕገ መንግሥቱ የተቋቋመ ሲሆን፣ በተጨማሪም ለተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች የሕገ መንግሥት አስተምህሮዎችን በመስጠት በማኅበረሰቡ ውስጥ ሕገ መንግሥታዊ ግንዛቤ እንዲፈጠር የበኩሉን አስተዋፅኦ በማበርከት ላይ ይገኛል፡፡

????????????????????????????????????